Success stories

አሕመድ አቡ ኻታላህ (በወንጀል ጥፋተኛ ተብሏል)

በ2005 ዓ.ም. በቤንጋዚ፣ ሊቢያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርን ጨምሮ የአራት አሜሪካዊያን ሞት፣

ወሮታ ለፍትሕ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርን ጨምሮ የአራት አሜሪካዊያንን ሕይወት ስለቀጠፈውን የ2005 ዓ.ም. የቤንጋዚ የአሜሪካ ልዩ ሚሲዮን ጥቃት ዋና ዕቅድ አውጪና ሽብርተኛ መሪ አሕመድ አቡ ኻታላህ በቁጥጥር ሥር መዋል እና በወንጀል ጥፋተኛ ለማስባል ያስቻለ መረጃ ለሰጠው ገልሰብ $3 ሚሊዮን ወሮታ ከፍሏል፡፡

በመረጃው ምንጭ የተሰጠን መረጃ በመጠቀም ኻታላህ በሰኔ 08 ቀን 2006 ዓ.ም. በሊቢያ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መጥቶ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ በኅዳር 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ክስ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በሰኔ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. የ22 ዓመት እስር ተፈርዶበታል፡፡ ወሮታ ለፍትሕ በቤንጋዚ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነት ያለባቸውን ሌሎች ሰዎች ወደ ፍትሕ ለማምጣት የሚያግዝ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

Skip to content