Success stories

ቶቲንግ ክራፍት ሃኖ (በወንጀል ጥፋተኛ ተብሏል)

በፊሊፒንስ የአሜሪካዊያን መታፈን እና መገደል፤
በፊሊፒንስ የአሜሪካዊያን መታፈን እና መገደል፤

ወሮታ ለፍትሕ በፊሊፒንስ፣ ለአቡ ሳያፍ ግሩፕ (ኤኤስጂ) ሽብርተኛ አባል ቶቲንግ ሃኖ በቁጥጥር ስር መዋል ምክንያት የሆነው መረጃ $100,000 ወሮታ ከፍሏል፡፡

ቶቲንግ ክራፍት ሃኖ የኤኤስጂ ቡድን አባል ነበር፤ ይህ ግለሰብ በግንቦት 19 ቀን 1993 ዓ.ም. በፊሊፒንስ፣ በፓላዋን ዶስ ፓልማስ ሪዞርት በሦስት አሜሪካዊያን ዜጎች አፈና ላይ ተሳትፏል፡፡ ሦስቱ አሜሪካዊያንም ጉዊሌርሞ ሶቤሮ እና የዩናይትድ ስቴትስ ሚሲዮን አባላት የትዳር አጋሮቹ ማርቲን እና ጋርሲያ በርንሃም ነበሩ፡፡ በሰኔ 04 ቀን 1993 ዓ.ም. የኤኤስጂ ቃል አቀባይ አቡ ሳያፍ፣ ጉዊሌርሞ ሶቤሮ ለፊሊፒንስ ፕሬዚደንት ግሎሪያ ማካፓጋል-አሮዮ የልደት ስጦታ እንዲሆን መገደሉን ገለጸ፡፡ በመስከረም 27 ቀን 1994 ዓ.ም. በባዚላን ደሴት የሰው አጽም ጭንቅላት ተገኘ፤ ይህ ጭንቅላት የሟች ጉዊሌርሞ ሶቤሮ መሆኑ ተረጋገጠ፡፡ በሰኔ 1994 ዓ.ም. ማርቲን በርንሃም በፊሊፒንስ ወታደሮች እና በኤኤስጂ መካከል በነበረው የተኩስ ልውውጥ ተገደለ፤ ጋርሲያ በርንሃም ብትቆስልም ለመትረፍ እና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመመለስ ችላለች፡፡

በታኅሳስ 28 ቀን 1997 ዓ.ም. የፊሊፒንስ የጸጥታ ኃይል በመረጃ ሰጪ ባገኘው መረጃ መሠረት ሃኖን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

Skip to content