የ1985 የዓለም የንግድ ማዕከል በተሽከርካሪ የተጠመደ ቦምብ ፍንዳታ
ወሮታ ለፍትሕ ፓኪስታናዊውን ሽብርተኛ ራምዚ አሕመድ ዮሱፍ ለመያዝ ላስቻለው መረጃ $2 ሚሊዮን ወሮታ ከፍሏል፡፡
ዮሱፍ ስድስት ሰዎችን ገድሎ ለ1000 ሰዎች መቁሰል ምክንያት የነበረውን የ1985 የዓለም የንግድ ማዕከል በተሽከርካሪ የተጠመደ ቦምብ ፍንዳታ ዋነኛ ጠንሳሽ ነበር፡፡ ቦምቡ በፈነዳ በሰዓታት ጊዜ ውስጥ ዮሰፍ በአውሮፕላን ወደ ፓኪስታን አመለጠ፡፡

ዮሱፍ ውስብስብ የሽብር ሴራ ይዞ ፊሊፒንስ ገባ፡፡ ዮሱፍ ዳግማዊ ጆን ፖል በፊሊፒንስ ጉብኝት በማድረግ ላይ ሳሉ ለመግደል ዕቅድ አወጣ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ደግሞ በእሲያ የአሜሪካን 12 የመንገደኞች አውሮፕላኖች አፈነዳ፡፡ ይህ ሴራ “ኦፕላን ቦጂንካ” የሚል ስም ተሰጠው፤ ይህ አባባል ደግሞ ወደ አረቢኛ ሲተረጎም “የፍንዳታ ኦፕሬሽን” ወይም “የታላቁ ፍንዳታ ኦፕሬሽን” ማለት ነው፡፡
ይህንን ዕቅድ ከመፈጸማቸው በፊት በታኅሳስ 28 ቀን 1987 ዓ.ም. ዮሱፍ እና ተባባሪው አብዱል ሃኪም አሊ ሃሺም ሙራድ በማኒላ በሚገኘው አማርታማቸው ውስጥ ሳሉ የኬሚካል ቅልቅል ደመና መሰል ጭጋግ ስለፈጠረ እና ይህም በአፓርታማው መስታወት ወደ ውጪ በመውጣቱ ቤታቸውን ትተው ሸሽተው ለመሄድ ተገደው ነበር፡፡ ዮሱፍም ሙራድ ወደ አፓርታማው ተመልሶ ላፕቶፕ እና ሌሎች ወንጀለኞች ሊያስብሏቸው የሚችሉ መረጃዎችን ይዞ እንዲመጣ ጠየቀው፡፡ ሙራድ ወደ አፓርታማው ሲመለስ ፖሊሶች በስፍራው ደርሰው ስለነበር አገኙት፡፡ ሙራድ እንደተያዘ ያወቀው ዮሱፍ ወደ ፓኪስታን አመለጠ፡፡
በጥር 1987 ዓ.ም. በክብሪት መያዣ ላይ ማስታወቂያ ያየ መረጃ ሰጪ እና ወሮታ ሊከፈለኝ ይችላል በሚል መነሳሳት በኢስላማባድ፣ ፓኪስታን የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ በማግኘት ዮሱፍ የት እንደሚገኝ ጥቆማ ሰጠ፡፡
በጥር 30 ቀን 1987 ዓ.ም. የፓኪስታን ባለሥልጣናት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማቲክ ደህንነት ልዩ ኤጀንቶች ደጋፍ ዮሱፍን በኢስላማባድ በቁጥጥር ስር አውለው በሽብር ክስ እንዲጠየቅ ለአሜሪካ አሳልፈው ሰጡት፡፡
ዮሱፍ ከሽብር ጋር በተያያዙ ሦስት የተለያዩ ክሶች ጥፋተኛ ሆኖ ተገኘ፡፡ በታኅሳስ 30 ቀን 1990 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ ዳኛ የዕድሜ ይፍታህ እና የ240 ዓመታት የእስር ቅጣት ፈርደውበታል፡፡
መረጃ ይስጡ
እርስዎ የበኩልዎን ያድርጉ፡፡ ደህንነቱ የተጠበቀ ዓለም እና ይበልጥ ብሩህ የወደፊት ጊዜን እውን ያድርጉ፡፡ ስለ ወሮታ ለፍትሕ መረጃ ማቀበያ ወይም ቅረቢያ አማራጮች ለማወቅ በዚህ ክሊክ ያድርጉ፡፡
- ታጋቺዎች/ተጠላፊዎች
- ሰሜን ኮሪያ
- ጣልቃገብነት በምርጫ ውስጥ
