Success stories

ሚር ኤይማል ካንሲ (የሞት ፍርድ ተፈጽሞበታል)

የአሜሪካዊያን ግድያ

ወሮታ ለፍትሕ በታኅሳስ 27 ቀን 1985 ዓ.ም. ሁለት በማዕከላዊ የመረጃ ኤጀንሲ (ሲአይኤ) ዋና መሥሪያ ቤት ወደሚገኘው ሥራቸው በመሄድ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ ተኩስ ከፍቶ ግድያ የፈጸመውን ሚር ኤይማል ካንሲ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ያስቻለ መረጃ ለሰጠ ግለሰብ ወሮታ ከፍሏል፡፡

ካንሲ በማዕከላዊ የመረጃ ኤጀንሲ (ሲአይኤ) ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት በሚገኝ የትራፊክ መብራት ቆመው በነበሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ያለ ማስጠንቀቂያ ወይም አንዳችም ትንኮሳ ሳይደረግበት ተኩስ ከፈተ፡፡

ካንሲ ይህንን ጥቃት እንደፈጸመ ወዲያውኑ ከዩናይትድ ስቴትስ ወጣ፤ በፓኪስታን ፑብጃብ በተባለ ክፍለ አገር በሰኔ 8 ቀን 1989 ዓ.ም. በቁጥጥር ስር እስኪውልም ድረስ ተፈላጊ ሆኖ ቆየ፡፡ ለፍርድ ለመቅረብም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተወሰደ፡፡

በኅዳር 01 ቀን 1990 ዓ.ም. ካንሲ በፌርፋክስ፣ ቨርጂኒያ ጁሪ የሲአይኤ ሠራተኞችን በመግደል ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ተገኘ፡፡ ካንሲ በኅዳር 05 ቀን 1995 ዓ.ም. የሞት ፍርድ ተፈጽሞበታል፡፡

Skip to content