ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ የሒዝባላ የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎችን ለማቃወስ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አሊ አል-ሻሃዒር የሂዝባላህ ገንዘብ አቅራቢ ሃሲብ ሙሐመድ ሃድዋን የቢሮ ኃላፊ በመሆን ያገለግላል፤ ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በሂዝባላህ ስም የገንዘብ መዋጮ ሲሰበስብ ቆይቷል፡፡ በሂዝባላህ ውስጥ ያሏቸው ተግባራት እና ኃላፊነቶች አካል በሆነ መልኩ፣ አል-,ሻሃዒር እና ሃድዋን ገንዘብ ወደ ሊባኖስ ለማስተላለፍ የዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሥርዓትን ቢጠቀሙም፣ ለማስተላለፉ ምክንያት የሆነውን ትክክለኛ ዓላማ ግን ይደብቃሉ፤ ዋናው ዓላማ የሽብር ድርጅቱን እንቅስቃሴዎች በገንዘብ መደገፍ ነው፡፡
በመስከረም 07 ቀን 2014 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አል-ስሃዒርን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ስሃዒር ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ስሃዒር ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
