ስለ ተቋሙ
አሁን ከተግባር ውጪ ሆነው 15 ሜይ ድርጅት የተመሠረተው በ1971 ነበር፡፡ ይህ ቡድን በአለም ዙሪያ የእስራኤል እና የአሜሪካን ዜጎች በመግደል እና የእስራኤል እና የአሜሪካ ጥቅሞች ላይ ጉዳት በማድረስ የፍልስጤምን ጥቅሞች አስከብራለሁ የሚል ነበር፡፡ 15 ሜይ ድርጅት ለበርካታ ጥቃቶች ኃላፊነት የወሰደ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል በነሐሴ 1974 ዓ.ም. የተፈጸመው የፓን አም በረራ 830 የቦምብ ጥቃት ይገኝበታል፤ በዚህ ጥቃት የ16 ዓመት ተሳፋሪ ሲገደል፣ 16 ሌሎች ላይ ደግሞ ጉዳት አስከትሏል፡፡
