ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በሚያዝያ 06 ቀን 1980 ዓ.ም. በኔፕልስ፣ ጣሊያን በዩኤስኦ ክለብ ላይ ለተፈጸመው የቦንብ ጥቃት ስለ ጁንዞ ኦኩዳይራ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ የቦንብ ፍንዳታው አንዲትን ሴት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደር ጨምሮ አምስት ሰዎች ሲገድል፣ 15 ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ ኦኩዳይራ የጃፓን ቀይ ሠራዊት የሽቡር ቡድን አባል ሲሆን፣ በሚያዝያ 01 ቀን 1985 ዓ.ም. በዩኤስኦ ክለብ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የቀረበበትን ክስ ይከላከል ተብሎ ተወስኖበታል፡፡ እንዲሁም ይህ ግለሰብ በሰኔ 1979 ዓ.ም. በሮም በዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ላይ ለተፈጸመው የተሽከርካሪ የቦንብ እና የሞርታር ጥቃት ተጠርጣሪ ነው፡፡
