ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ኩርዲስታን ሰራተኞች ፓርቲ (ፒኬኬ) በሌላ ስሙ ኮንግራ – ጄል ከፍተኛ መሪ ዱራን ካልካን መረጃ ለሚሰጥ እስከ $3 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ፒኬኬ በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት (ኤፍቲኦ) ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ካልካን የፒኬኬ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሲሆን በታኅሳስ 2002 ዓ.ም. ሰባት የቱርክ ወታደሮችን ለገደለው ጥቃት ተጠያቂ ነው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የየገንዘብ ሚኒስቴር ካልካን ልዩ የናርኮቲክ ህገወጥ አዘዋዋሪ (ኤስዲኤንኬ) ተብሎ በሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም. በወጣው የውጭ አገራት ናርኮቲክሰ መሪ አሰያየም ህግ (ኪንግፒን አክት) መሰረት ተሰይሟል፡፡
