ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ኢዘዲን አብደል አዚዝ ኸሊል፣ ይበልጥ የሚታወቅበት ስም ያሲን አል-ሱሪ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $3 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
አል-ሱሪ በኢራን የሚገኝ የአል-ቃዒዳ አመቻች ነው፡፡ አል-ሱሪ የአል-ቃዒዳን ከፍተኛ አመራር ለመደገፍ ከመላው መካከለኛው ምሥራቅ ወደ ኢራን ከዚያ ወደ ፓኪስታን ገንዘብ እና ምልምሎችን አንቀሳቅሷል፡፡ የኢራን ባለሥልጣናት ከአል-ሱሪ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ከ1997 ጀምሮ በኢራን ድንበር ውስጥ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ፈቃድ ሰጥተውታል፡፡ ቀደም ብሎ አል-ሱሪን የሚመለከተቱ መረጃዎች እንዲቀርቡ በወሮታ ለፍትሕ እርሱን ማሰወቂያ ከተነገረ በኋላ በታኅሳስ 2004 ዓ.ም አል-ሱሪ በኢራን መንግሥት በቁጥጥር ስር ውሎ ነበር፡፡
በሐምሌ 21 ቀን 2003 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አል-ሱኒን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ሱኒ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ሱኒ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አል-ቃዒዳ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
