ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ፓን አም የበረራ 73 ጠለፋ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በነሐሴ 30 ቀን 1978 ዓ.ም. አቡ ኒዳል ድርጅት የሚባለው ሽብርተኛ ድርጅት ተጠርጣሪ አባላት በካራቺ፣ ፓኪስታን 379 ተሳፋሪዎችን ይዞ የነበረ አውሮፕላን መሬት ሳለ ጠለፉ፡፡ ተሳፋሪዎችን እና የበረራ ሠራተኞችን ከሞላ ጎደል ለ16 ሰዓታት አግተው ካቆዩ በኋላ፣ በጭፍን ተኩስ ከፈቱ፡፡ በዚህም ሁለት አሜሪካዊያንን ጨምሮ ሃያ ሰዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡

በጠለፋው የተሳተፉ አምስት ሽብርተኞች የኋላ ኋላ ተይዘው፣ በፓኪስታን ፍርድ ቤት ቀርበው የእስር ቅጣት ተጥሎባቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ጥፋተኛ ከተባሉት እነዚህ አምስት ተከሳሾች አራቱ በጥር 2000 ዓ.ም ከእስር እንደተለቀቁ ተነግሯል፤ አሁንም በነጻነት ይንቀሳቀሳሉ፡፡ እያንዳንዳቸው በዩናይትድ ስቴትስ ግራንድ ጁሪ ክስ ይመስረትባቸው ተብሎ ተወስኖባቸዋል፤ በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ ሽብረተኞች ዝርዝር ውስጥም ስማቸው ይገኛል፡፡ ወሮታ ለፍትሕ በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ሰው ላይ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
-ዋዳዉድ መሐመድ ሃፊዝ አል-ቱርኪ -ጀማል ሰዒድ አብዱል ራሂም -ሙሃመድ አብዱላህ ኸሊል ሁሴን አር-ራሃያል -ሙሐመድ አሕመድ አል-ሙናዋር
