ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ፒተር ኪልበርን ግድያ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ኪልበርን በቤይሩት አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ የቤተ መጽሐፍት ሠራተኛ ነበር፡፡ በኅዳር 24 ቀን 1977 ዓ.ም. ይህ ግለሰብ መጥፋቱ ተነገረ፡፡ ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ አስከሬኑ ከሌሎች ሁለት ምርኮኞች ጋር ተገኘ፡፡ ታጋቾቹ ማቾች በጥይት ከተመቱ በኋላ በተራራማው ምሥራቃዊ ቤይሩት ተጣሉ፡፡ ኪልበርን ለአስር ዓመታት ያህል በቆየው የሊባኖስ የእገታ ቀውስ በአብዛኛው የምዕራባዊያን አገራት ዜጎች ከነበሩ፣ በሂዝባላህ እና ከሂዝባላህ ጋር ግንኙነት በነበራቸው ሽብርተኞች ከታገቱ 100 ተጎጂዎች መካከል አንዱ ነበር፡፡
