የጆኤል ሽሩም ግድያ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ አሜሪካ ዜጋ ጆኤል ሽሩም ግድያ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በመጋቢት 09 ቀን 2004 ዓ.ም. ይህ የ29 ዓመት ዕድሜ የነበረው ይህ ግለሰብ በታይዝ፣ የመን ወደ ሥራ በመሄድ ላይ እያለ ሞተር ሳይክል ይዞ የነበረ ታጣቂ በእርሱ ተሽከርካሪ ጎን ሞተር ሳይክሉን አቁሞ ተኩሶ ገድሎታል፡፡ ጥቃቱ ከተፈጸመ ከጥቂት ቀናት በኋላ የአረብ ባሕረሰላጤ አል-ቃዒዳ (ኤኪውኤፒ) ለግድያው ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡

በሞተበት ጊዜ ሽሩም በዓለም ዓቀፍ ሥልጠና እና ልማት ማዕከል አስተዳዳሪ እና የእንግሊዝኛ መምህር ሆኖ ይሰራ ነበር፡፡ ከባለቤቱ እና ከሁለት ሕጻናት ልጆቹ ጋር በየመን ነዋሪ ነበር፡፡

Skip to content