የዳንኤል ፐርል አፈና እና ግድያ

ደቡብ እና መካከለኛው እስያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ዳንኤል ፐርል እገታ እና ግድያ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ፐርል የተባለው የዎል ስትሪት ጋዜጣ የደቡብ እሲያ ቢሮ ኃላፊ በጥር 15 ቀን 1994 ዓ.ም. በካራቺ፣ ፓኪስታን ታገተ፡፡ በየካቲት 1994 ዓ.ም. የእርሱን ግድያ የሚያመላክት ቪድዮ በኢንተርኔት ተለጥፎ ነበር፡፡ የፐርል አስከሬን በግንቦት 1994 ዓ.ም. ተገኝቶ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተመልሷል፡፡

በሰኔ 1994 ዓ.ም. አሕመድ ኡመር ሰዒድ ሼክ በእገታ እና እገታ ለመፈጸም በመመሳጠር፣ በዚህም ምክንያት በፐርል ግድያ፣ በ1986 ዓ.ም. ደግሞ በሕንድ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ እገታ ምክንያት የተመሰረተባቸውን ክስ ይከላከል የሚል ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡ በሐምሌ 08 ቀን 1994 ዓ.ም. ሼክ እና ሦስት ሌሎች ተጠርጣሪዎች በፓኪክታን በወንጀል ጥፋተኞች ተብለው የሞት ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡

በጥር 2013 ዓ.ም. የፓኪስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፐርል እገታ እና ግድያ ላይ በተሳተፉት ላይ ከቀረበባቸው ክስ ነጻ አድርጓቸዋል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ሼክን ተጠያቂ ለማድረግ ለወሰደችው እርምጃ ዕውቅና ትሰጣለች፤ ሼክ በፓኪስታን ሕግ መሠረት አሁንም በቁጥጥር ሥር መሆኑንም ታውቃለች፡፡ ፍትሕ መደረጉን ለማረጋገጥም የፓኪስታን መንግሥት ያሉትን የሕግ አማራጮች እንዲፈትሽ ይጠበቅበታል፡፡ ዩናይትድ ስቴትስም ሼክ በአሜሪካ ዜጋ ላይ ለፈጸመው እጀግ ሰቅጣጭ ወንጀል ክስ ልታቀርብበት ዝግጁ ናት፡፡

Skip to content