የሌተር ቦምብ ክስተቶች

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ | ምዕራባዊ ንፍቀ ክበብ | አውሮፓ እና ዩራሺያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሌተር ቦምብ ክስተቶች መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በታኅሳስ 1989 ዓ.ም. እና በጥር 1989 ዓ.ም. መካከል፣ የበዓል መልካም ምኞት መግለጫ መስለው የተሰሩ 16 ሌተር ቦምቦች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እና ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በፖስታ ተደርገው ተልከዋል፡፡

ከእነዚህ ሌተር ቦምቦች መካከል 13 በኒው ዮርክ ከተማ፣ ዋሽንግተን ዲሲ እና ለንደን በአል-ሃያት ጋዜጣ መሥሪያ ቤቶች ደርሰዋል፡፡ አንድ ቦምብ በለንደን ሲፈንዳ፣ ሁለት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል፡፡ ሌሎች ሦስት የሌተር ቦምቦች ደግሞ በዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ማረሚያ ቤት፣ ሌቨንወርዝ፣ ካንሳስ ተገኝተዋል፡፡

እያንደንዳቸው የደብዳቤ ቦምቦች ታኅሳስ 12 ቀን 1989 ዓ.ም.፣ ግብጽ፣ አሌክሳንድሪያ የሚል መለያ የያዙ ናቸው፤ ማናቸውም ቢሆኑ የመመለሻ አድራሻ የያዙ አልነበሩም፡፡ ቦምቦቹ ሁሉ በነጭ ፖስታ ውስጥ ተደርገው በኮምፒውተር የተዘጋጀ አድራሻ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ምልክቶች የነበሯቸው ናቸው፡፡

Skip to content