ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በ1985 ዓ.ም. በኒው ዮርክ ከተማ በዓለም የንግድ ማዕከል ላይ ስለተፈጸመው የቦምብ ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በየካቲት 19 ቀን 1985 ዓ.ም. ሽብርተኞች 1,500 ፖውንድ መጠን ያለው በተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦምብ በዓለም የንግድ ማዕከል የተሽከርካሪ መቆሚያ አፈነዱ፡፡ ይህ ፍንዳታ ስድስት ሰዎችን ሲገድል፣ ከ1000 በላይ የሆኑትን ደግሞ አቁስሏል፡፡ በመቶ ሚሊዮን የሚቀጠር የንብረት ጉዳትም አስከትሏል፡፡

ያሲን እና ራምዚ ዮሱፍ የተባለውን ገልሰብ ጨምሮ ከአል-ቃዒዳ (ኤኪው) ጋር ግንኙነት የነበራቸው ግለሰቦች ቡድን ጥቃቱን ለመፈጸም ዕቅድ አወጣ፡፡ ከፍተኛ የአል-ቃዒዳ አባል እና የዮሱፍ አጎት ኻሊድ ሼክ መሐመድ ደግሞ ለዚህ ሥራ የሚሆን ገንዘብ አቀረበ፡፡ የጥቃቱ ፈጻሚዎች ተስፋ ያደረጉት ቦምቡ ሕንጻውን እንደሚያፈርሰው ነበር፤ ሕንጻው ሲፈርስ ድግሞ ፍርስራሹ ሁለተኛውን ሁለተኛውን ሕንጻ ይጥለዋል የሚል ተስፋ ነበራቸው፡፡ ከተመሳጣሪዎቹ መካከል ስድስቱ ዋናውን የሃሳቡን አመንጪ ራምዚ ዮሱፍ ጨምሮ በቁጥጥር ስር ውለው፣ በፍርድ ቤት ቀርበው፣ ጥፋተኞች ሆነው በመገኘታቸው የዕድሜ ይፍታህ ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡ ሰባተኛው ተመሳጣሪ አብዱል ራህማን ያሲን (ሃይፐርሊንክ) እስከ አሁን አልተገኘም፡፡
