የአሜሪካዊያን ዜጎች አፈና እና ግድያ

ምዕራባዊ ንፍቀ ክበብ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በ1995 ዓ.ም. በኮሎምቢያ በዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ላይ ስለተፈጸመው እገታ እና ግድያ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በየካቲት 06 ቀን 1995 ዓ.ም. በጸረ-ዕጽ ተልዕኮ ላይ የነበረ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አውሮፕላን በካኩዌታ፣ ኮሎምቢያ ክራሽ ላንድ አደረገ፡፡ የኮሎምቢያ አቢዮታዊ የጦር ኃይል ወይም ሪቮሉሽነሪ አርምድ ፎርስስ ኦፍ ኮሎምቢያ (ኤፍኤአርሲ) የተባለ የግራ ክንፍ አማጺ ቡድን አባላት በአሜሪካው ዜጋ ቶማስ ጃኒስ እና የኮሎምቢያው ሳጅን ሉዊስ አልሲዴስ ክሩዝ ላይ ግድያ ፈጸሙ፡፡ አማጺያኑ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ ሌሎች ማርክ ጎንሳልቭስ፣ ቶማስ ሆዌስ እና ኬኔት ስታንሴል የተባሉ ሌሎች ሦስት የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን በታጋችነት ወስደዋል፡፡

Skip to content