ዩኒየን ቴክሳስ ፔትሮሊየም ግድያዎች

ደቡብ እና መካከለኛው እስያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ዩኒየን ቴክሳስ ፔትሮሊየም (ዩቲፒ) ግድያዎች መረጃ ለሚሰጥ እስከ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በኅዳር 03 ቀን 1990 ዓ.ም. አራት የዩቲፒ ሠራተኞች በካራቺ፣ ፓኪስታን ወደ ሥራ በመሄድ ላይ ነበሩ፡፡ የነበሩበት ስቴሽን ዋገን ወደዩቲፒ ቢሮ ሕንጻ የሚወስደውን ድልድይ እንዳለፈ ሁለት ታጣቂዎች ከቀይ ሆንዳ ሲቪክ መኪና ዘልለው በመውጣት እነርሱ በነበሩበት መኪና ላይ የተኩስ እሩምታ ከፈቱ፡፡ በዚህ ጥቃት ሁሉም የዩናይትድ ስቴትስ ሠራተኞች እና ፓኪስታናዊው ሾፌራቸው ተገደሉ፡፡

ይህ ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ፍርድ ቤት በሚር አይማል ካንሲ ላይ ከሁለት ቀናት አስቀድሞ የጥፋተኝነት ውሳኔ በማስተላለፉ ላዚያ የተሰጠ የአጸፋ ምላሽ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ካንሲ በ1985 ዓ.ም. በላንግሌ፣ ቨርጂኒያ ዋና መሥሪያ ቤት አጠገብ በሁለት የሲአይኤ ሠራተኞች ላይ ለተፈጸመው ግድያ ተጠያቂ ነው፡፡

Skip to content