የባሕር ኃይል የጦር ሰፈር ጥቃት

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በ1976 ዓ.ም. በቤይሩት፣ ሊባኖስ በዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ኃይል የጦር ሰፈር ላይ ስለተፈጸመው የቦንብ ጥቃት መረጃ ለሚስጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በጥቅምት 12 ቀን 1976 ዓ.ም. በሊባኖስ፣ በቤሩት ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ በነበሩ የዩናይትድ ስቴትስ እና የፈረንሳይ ሕብረብሔር ጦር ላይ በተሽከርካሪ የተጠመደ ቦምብ ፈነዳ፡፡ ይህ ሕብረብሔር ጦር በሊባኖስ የተሰማራው ዓለም ዓቀፍ ሰላም የማስጠበቅ ጥረት አካል በሆነ መልኩ ነበር፡፡ በዚህ ጥቃት 241 የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ሲሞቱ 128ቱ ደግሞ ቆስለዋል፡፡ በዚያው ቀን በተመሳሳይ ጥቃት 58 ወታደሮች ሞተዋል፡፡ ይህንን ጥቃት ያስተባበረው ሂዝባላህ ራሱ ነው ተብሎ ይታመናል፤ ለዚህም ከኢራን ድጋፍ እና ገንዘብ አግኝቷል፡፡

Skip to content