ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በማንኛውም አገር ውስጥ የሚገኝን ማንኛውም በሻኬል ኻን ላይ ግድያ ስለፈጸመው፣ ሙከራ ስላደረገ ወይም ይህንን ለመፈጸም ስለተመሳጠረ ወይም እገዛ ስላደረገ ሰው መረጃ ለሚሰጠት ሰው እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
በመጋቢት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ምሽት፣ በዩናይትድ ስቴትስ ሕጋዊ ነዋሪ እና የሬስቶራንት ባለቤት የነበረው ኻን በጆንሰን ከተማ፣ ኒው ዮርክ ከሬስቶራንቱ ደጅ የሞት ፍርድ በሚፈጸምበት ሁኔታ ተገድሎ ተገኝቷል፡፡ ኻን ለምሽቱ መደብሩን በመዝጋት ላይ ሳለ በአንድ የጦር መሣሪያ በያዘ ሰው ተተኩሶበት ሕወቱን አጥቷል፡፡
ይህ የ50 ዓመት ዕድሜ የነበረው ኻን በፓኪስታን የስዋት ክልል ተወላጅ የነበረሲሆን፣ በዚያ አገር የሽብር ድርጅቶችን በግልጽ በሚቃወሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ተሳትፎ ነበረው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የኒውዮርክ ሰሜናዊ ዲስትሪክት አቃቤ ህግ ቢሮ እና የኤፍቢአይ የጋራ የሽብር ግብረ ሃይል ግድያውን በማጣራት ላይ ናቸው።
