ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ዩናይትድ ስቴትስ ከ1974 ዓ.ም. እስከ 1984 ዓ.ም. በሊባኖስ ውስጥ በአሜሪካዊያን እና በሌባኖሳዊያን ላይ ስለ ተፈጸመው እገታ እና ግድያ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በዚህ ወቅት ሂዝባላህ እና ከሂዝባላህ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሽብርተኞች 100 ያህል በአብዛኛው የምዕራብ አገራት ዜጎችን አገተ፡፡ ከታጋቾችም መካከል፣ አሜሪካዊያኑ ዊሊያም በርክሌይ ፒተር ኪልበርን እና ዊሊያም ሂግንስ ስቃይ ተፈጽሞባቸው ተገድለዋል፡፡

ዊሊያም በርክሌይ በሊባኖስ የሲአይኤ ጣቢያ ኃላፊ ነበር፤ ይህንን ኃላፊነት በበጎ ፈቃደኝነት የተቀበለው በ1975 ዓ.ም. በሊባኖስ የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጽሞ 17 አሜሪካዊያንን ጨምሮ 63 ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ነበር፡፡ በርክሌ ሲመረመር እና ሰቆቃ ሲፈጸምበት ቆይቶ በግንቦት 26 ቀን 1977 ዓ.ም. በእስር ላይ እያለ ሞተ፡፡
ፒተር ኪልበርን በቤይሩት በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የቤተ መጽሐፍት ሠራተኛ ነበር፡፡ በኅዳር 24 ቀን 1977 ዓ.ም. መጥፋቱ ተነገረ፡፡ ከአስራ ስድስት ወራት በኋላ አስከሬኑ ከሌሎች ሁለት ምርኮኞች ጋር ተገኘ፡፡ አሳሪዎቹም እርሱን ከመግደላቸው በፊት ሲያሰቃዩት እና ሲመረምሩት ነበሩ፡፡
የአሜሪካ ባሕር ኃይል ጓድ የነበረው ኮሎኔል ዊሊያም በደቡብ ሊባኖስ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባል ሳለ በየካቲት 09 ቀን 1980 ዓ.ም. ታገተ፡፡ አጋቾቹ ሂግንስን ከመግደላቸው በፊት ምርመራ አካሂደውበት እና ሰቆቃ ፈጽመውበት ነበር፡፡
