ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ የሂዝባላን የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎች ለማሰናከል የሚያስቸል መረጃ ለሚሰጥ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሂዝባላ ኦፕሬሽኖቹን ለማስቀጠል እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ጥቃቶቹን ለመፈጸም የፋይናንስ እና የማመቻቸት (ፋሲሊቴሽን) ኔትወርኮች ይጠቀማል፡፡ ሂዝባላ ከኢራን፣ ከዓለም ዓቀፍ የንግድ ሥራዎች፣ ከረጂዎች ኔትወርክ፣ ከሙስና እና የገንዘብ ሕገወጥ ዝውውር በዓመት እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያገኛል፡፡
ሂዝባላ በዓለም ዙሪያ የሚፈጽማቸውን ሰይጣናዊ ተግባራት ለመደገፍ ገንዘብ ይጠቀማል፤ ከተግባራቱም መካከል የአሳድን አምባገነናዊ ሥርዓት ለመደገፍ በሶሪያ የሚሊሻ አባላትን ማሰማራት፤ ሰርቬላንስ ለማካሄድ እና በዩናይትድ ስቴትስ መረጃ ለመሰብሰብ መንቀሳቀስ እንዲሁም ሂዝባላህ ዒላማ የሚመታ ሚሳኤል እንዲኖረው እስከማድረግ ድረስ የሂዝባላህን ወታደራዊ አቅም መገንባት፡፡ እነዚህ የሽብርተኞች ድርጊቶች የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙት በሂዝባላ ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ደጋፊዎች ኔትወርክ እና እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ነው፤ እነርሱም ቡድኑ በፋይናንስ የማድረግ አቅም እንዲኖረው እና ለቡድኑ ሕይወት የሚሰጥ መሠረተ ልማት ናቸው፡፡ ሂዝባላህ ከኢራን ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሣሪያ፣ ሥልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ ያገኛል፤ የኢራን መንግሥት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሽብርተኝነትን የሚደግፍ መንግሥት ተብሎ ተሰይሟል፡፡
በመስከረም 28 ቀን 1990 ዓ.ም. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ እንደተሻሻለው፣ በክፍል 219 ስር ሂዝባላህን በውጭ አገር የሚገኝ የሽብር ድርጅት በማለት ሰይሟል፡፡ በጥቅምት 21 ቀን 1994 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂዝባላህን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሂዝባላህ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሂዝባላህ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሂዝባላህ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ የሚከተሉት እንዲታወቁ እና ለማሰናከል የሚያስችሉ መረጃዎች ለሚሰጡ ወሮታ ይፍላል ፡-
- ለድርጅቱ ወይም ለቁልፍ የፋይናንስ ማመቻቻ ዘዴዎቹ ከፍተኛ የፋናንስ ገቢ ምንጮች፤
- ዋና ዋና የሂዝባላህ ረጂዎች እና የፋይናንስ አመቻቺዎች፤
- ከፍተኛ የሚባሉ የሂዝባላህ ረጂዎች እና የፋይናንስ አመቻዊዎች፤
- ከፍተኛ የሚባሉ የሂዝባላህን ልውውጦች እያወቁ የሚያካሂዱ የፋይናንስ ተቋማት እና የልውውጥ ቤቶች፤
- በዓለም ዓቀፍ ድርብ ጥቅም የሚሰጡ ቴክኖሎጂዎች ግዢ ላይ የሚሳተፉ ኩባንያዎች፤
- ድርጅቱን በፋይናንስ የሚደግፉ የሂዝባላ አባላት እና ደጋፊዎች የሚሳተፉባቸው የወንጀል ዕቅዶች
