ዋሊድ መሐመድ ሙስጠፋ ጃዳላህ

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ሐማስ ተብሎ የሚታወቀውን ሽብርተኛ ድርጅት ወይም በሌላ ስሙ ሃረካት አል-ሙቃዋማ አል-ኢስላሚያ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

ዋሊድ መሐመድ ሙስጠፋ ጃዳላህ የዮርዳኖስ ዜጋ ሲሆን፣ የሐማስ ጀሌ እና የሐማስ ኢንቬስትመንት ኔትወርክ አባል ነው፡፡ በቱርክ ነዋሪ ሲሆን፣ በበርከታ የሃማስ ኢንቬስትመንት ኩባንያዎች ቦርድ ውስጥ ይሰራል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቅምት 07 ቀን 2016 ዓ.ም. በሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ (ኤግዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224፣ እንደተሻሻለው ጃዳላህን ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በማለት ሰይሞታል፡፡ በዚህ መልኩ መሰየሙም የሽብር ጥቃት በሚፈጽሙ ወይም ከፍተኛ የመፈጸም ዕድል ያላቸውን የውጭ አገር ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች ላይ ዕግድ ይጥላል፡፡ ከዚህም ሌላ ይህ ትዕዛዝ የዩይነትድ ስቴትስ መንግሥት በዚህ ትዕዛዝ ስር ሽብርተኞች እና የሽብር ድርጅቶች ተብለው ለተሰየሙት ወይም ለእነርሱ የበታች ድርጅቶች፣ ሽፋን ሰጪዎች፣ ወኪሎች ወይም ተባባሪዎች ድጋፍ፣ አገልግሎቶች ወይም እገዛ የሚሰጡትን ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች እንዲያግድ የሚያዝ ነው፡፡

Skip to content