ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ የኢራን ኢስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ሠራዊት (አይአርጂሲ) (ሃይፐርሊንክ) እና አይአርጂሲ-ቆድስ ኃይልን አካትቶ (አይአርጂሲ-ኪውኤፍ) (ሃይፐርሊንክ) የልዩ ልዩ ቅርንጫፎቹን የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎች ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $15 ሚሊዮን ይከፍላል፡፡ አይአርጂሲ በዓለም ዙሪያ በርካታ የሽብር ጥቃቶችን እና እንቅስቃሴዎችን በገንዘብ ደግፏል፡፡ አይአርጂሲ-ኪውኤፍ እንደ ሃማስ፣ ሂዝባላህ እና በኢራቅ የሚገኙ በኢራን የሚደገፉ የመሳሰሉ ቡድኖችን በመጠቀም የኢራንን የሽብር ተግባራት ይመራል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለኢራን ኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት፣ ስለኢራን ኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት-ቆድስ (አይአርጂሲ-ኪውኤፍ)፣ ስለ ቅርንጫፎቹ ወይም ስለቁልፍ የፋይናንስ ማመቻቻ ዘዴዎቹ እና ከዚህ በማስከተል ስለተዘረዘሩት መረጃ ለሚሰጥ ወሮታ ይከፈላል፡-
- የኢራን ኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት ሕገወጥ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎች ለምሳሌ ነዳጅ-ለገንዘብ፤
- አይአርጂሲን በመወከል በዓለም ዓቀፍ እንቅስቃሴዎች የሚሳተፉ ሽፋን ሰጪ ኩባንያዎች፤
- ለአይአርጂሲ እገዛ የሚያደርጉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች፤
- ከአይአርጂሲ ጋር የሥራ ግንኙነት ያላቸው ይፋዊ የፋይናንስ ተቋማት፤
- አይአርጂሲ ገንዘብ እና ማቴሪያል ለሽብርተኛ እና ሚሊሻ ተላላኪዎቹ እና አጋሮቹ የሚያስተላልፍበት መንገድ፤
- የአይአርጂሲ ረጂዎች ወይም የፋይናንስ አመቻቾች፤
- የአይአርጂሲ ልውውጦችን የሚያመቻቹ የፋይናንስ ተቋማት እና የልውውጥ ተቋማት፤
- በአይአርጂሲ ወይም በእርሱ ገንዘብ አቅራቢዎች ባለቤትነት ስር ያሉ የንግድ ድርጅቶች ወይም ኢንቬስትመንቶች፤
- ስለአይአርጂሲ በመሆን ድርብ ጥቅም ያላቸውን ቴክኖሎጂዎች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚገዙ ሽፋን ሰጪ ኩባንያዎች፤
- ድርጅቱን በፋይናንስ የሚጠቅሙ የአይአርጂሲ አባላትን እና ደጋፊዎችን ያካተቱ የወንጀል ዕቅዶች፡፡
በ1971 ዓ.ም. ከኢራን አቢዮት በኋላ የተመሠረተው የኢራን ኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ የኢራን ወታደራዊ ሠራዊት አንድ ክፍል ነው፡፡ በቁድስ ኃይል አማካኝነት ይህ ሠራዊት የኢራን መንግሥትን ዓለም ዓቀፍ የሽብር ዘመቻዎች የመምራት እና የመፈጸም ሚና ይጫወታል፡፡
የኢራን የአቢዮት ጥበቃ ሠራዊት በዓለም ዙሪያ የሽብር ዕቅዶች በማውጣት እና በመደገፍ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ቆይቷል፡፡ የኢራን የአቢዮት ጥበቃ ሠራዊት በአፍጋኒስታን እና በኢራቅ በዩናይትድ ስቴትስ እና በጥምር ጦሩ እንዲሁም በዲፕሎማሲያዊ ሚሲዮኖች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ደግፏል፡፡
በተጨማሪም፣ የኢራን አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት በርካታ ቁጥር ያላቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች አግቷል፣ በስህተት አስሯል፤ በርካቶቹ ዛሬም በኢራን ይገኛሉ፡፡
የኢራን የአቢዮት ጥበቃ ሠራዊት-ኪውኤፍ በዓለም ዙሪያ በርካታ የሽብር ጥቃቶች አቅዷል፤ ከእነርሱም መካከል ባሕሬይን፣ ቦስኒያ፣ ቡልጋሪያ፣ ጀርመን፣ ኬኒያ፣ ቱርክ እና ዩናይትድ ስቴትስ ይገኙባቸዋል፡፡
በሚያዝያ 07 ቀን 2011 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ እንደተሻሻለው በክፍል 219 መሠረት አይአርጂሲን በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ በማለት ሰይሞታል፡፡ በ2009 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አይአርጂሲን ልዩ ዓለም ዓቀፍ አሸባሪ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአይአርጂሲ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአይአርጂሲ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ለዚህ ቡድን ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
