ኢብራሂም አቂል

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 7 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ የሒዝቦላ ቁልፍ መሪ ስለነበረው ኢብራሒም አቂል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $7 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

ኢብራሒም አቂል ወይም ሌላ ስሙ ታህሲን፣ የሒዝቦላ ከፍተኛ ወታደራዊ አካል በሆነው ጂሀድ ምክር ቤት ውስጥ ያገለግላል፡፡

በ1970ዎቹ አቂል የሒዝባላ የሽብር ሕዋስ በሆነው ኢስላሚክ ጅሃድ ኦርጋናይዜሽን (ወይም የኢስላማዊ ጂሃድ ድርጅት) ውስጥ ዋነኛ አባል ነው፤ ይህ ሕዋስ ለ63 ሰዎች ሞት ምክንያት ለነበረው በቤይሩት የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የሚያዝያ 1975 ዓ.ም. ጥቃት እና በጥቅምት 1976 ዓ.ም. ደግሞ ለ241 የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችን ሕይወት የቀጠፈው በዩናይትድ የባሕር ኃይል የጦር ሰፈር የቦንብ ጥቃቶች ኃላፊነት ወስዷል፡፡

በ1970ዎቹ፣ አቂል በሌባኖስ አሜሪካዊያን እና የጀርመን ዜጎችን እገታ መርቷል፣ በዚያም ይዞ አቆይቷቸዋል፡፡

በሐምሌ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. የዩናይትስ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አቂልን በሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ ቁጥር 13582 መሠረት ለሒዝቦላ ወይም ስለሒዝቦላ ድርጅት በመንቀሳቀስ ምክንያት ፈርጆታል፡፡ ከዚያ በመቀጠል በጳጉሜን 05 ቀን 2011 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ 13224፣ እንደተሻሻለው አቂልን ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በማለት ሰይሞታል፡፡

Skip to content