ስለ ተቋሙ
የእስላማዊ መንግሥት የኮራሳን ክልል (አይሲስ-ኬ) በአፍጋኒስታን የሚገኝ የሽብር ድርጅት ሲሆን፣ እርሱም በአፍጋኒስታን እና በፓኪስታን ኦፕሬሽኖች ያካሂዳል፡፡ ይህ ድርጅት በዋናነት በቀድሞ ተኽሪቅ-ኢ ታሊባን ፓኪስታን፣ አፍጋን ታሊባን እና በኡዝቤኪስታን እስላማዊ እንቅስቃሴ የተመሠረተ ነበር፡፡ አይሲስ-ኬ በ2007 ዓ.ም. ለአይሲስ ያለውን ታማኝነት ገልጾዋል፡፡ አይሲስ-ኬ በሐምሌ 2008 ዓ.ም. በካቡል ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ፈጻሚ ነው፡፡ ይህ ጥቃት 80 ያህል ሰዎችን ሲገድል 230ቹን ደግሞ አቁስሏል፡፡ በነሐሴ 2008 ዓ.ም. ይህ ቡድን በኩዌታ፣ ፓኪስታን ለተፈጸመው እና የ94 ሰዎችን ሕይወት ለቀጠፈው ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አይሲስ-ኬ ሕጻናትን እና እናቶቻቸውን ጨምሮ 24 ሰዎችን ለገደለው በካቡል ሆስታል ለተፈጸመ ጥቃት በኃላፊነት ይጠየቃል፡፡
በጥር 05 ቀን 2008 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይሲስ-ኬን በምዕራብ አፍሪካን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ቀደም ሲል በመስከረም 18 ቀን 2006 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይሲስ-ኬን ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአይሲስ-ኬ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአይሲስ-ኬ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አይሲስ-ኬ በምዕራብ አፍሪካ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
