ስለ ተቋሙ
ኢስላማዊ መንግሥት በምዕራብ አፍሪካ (አይሲስ–ደብልዩኤ) ቦኮ ሃራም የተሰኘው ሽብርተኛ ድርጅት አንጃ ሲሆን፣ ይህ ድርጅት የተመሠረተው አይሲስ በምዕራብ አፍሪካ በመጋቢት 2007 ዓ.ም. ለአይሲስ ታማኝነቱን ሲገልጽ ነበር፡፡ አይሲስም የዚህን ቡድን ታማኝነት በመቀበል ራሱን አይሲስ በምዕራብ አፍሪካ ብሎ መጥራት ጀመረ፡፡ ይህ ድርጅት በዋናነት በሰሜን ምሥራቅ ናይጄሪያ እና በቻድ ሃይቅ ክልል ይንቀሳቀሳል፤ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮም በርካታ የሽብር ጥቃቶች ፈጽሟል፡፡ በኅዳር 2010 ዓ.ም. አይሲስ በምዕራፍ አፍሪካ በቻድ እና በናይጄሪያ ለተፈጸሙ አምስት ጥቃቶች ኃላፊነቱን ወስዷል፤ በእነዚህ ጥቃቶች 118 ሰዎች ሞተዋል፡፡ በግንቦት 2011 ዓ.ም. አይሲስ በምዕራብ አፍሪካ በምዕራብ ኒጀር ለተፈጸሙት እና 29 ወታደሮችን ለገደሉት ሁለት ጥቃቶች ኃላፊነት ወስዷል፡፡ በሐምሌ 2011 ዓ.ም. የአይሲስ በምዕራብ አፍሪካ ተዋጊዎች 20 የናይጄሪያ እና አምስት የቻድ ወታደሮችን ገድለዋል፤ ይህም የሆነው በባጋ አቅራቢያ፣ የናይጄሪያ ወታደራዊ ሰፈር ላይ ጥቃት በተፈጸመበት ወቅት ነበር፡፡
በየካቲት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይሲስ በምዕራብ አፍሪካን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ቀደም ሲል በየካቲት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይሲስ በምዕራብ አፍሪካ ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአይሲስ በምዕራብ አፍሪካ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአይሲስ በምዕራብ አፍሪካ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አይሲስ በምዕራብ አፍሪካ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
