ስለ ተቋሙ
አንሳር አል-ዳይን (ኤኤዲ) በተመሠረተው በ2003 ዓ.ም. ማብቂያ ነበር፡፡ የማሊ መንግሥት በመጋቢት 2004 ዓ.ም. ከተጣለ በኋላ፣ ኤኤዲ ማሊን ከተቆጣጠሩ ድርጅቶች መካከል አንዱ ነበር፤ ይህም ድርጅት በዩኔስኮ የተመዘገቡ የዓለም የቅርስ ስፍራዎችን አውድሟል፣ በቁጥጥሩ ስር ባሉ ስፍራዎችም እጅግ ጥብቅ የሆነ የሸሪዓ ሕግ ተፈጻሚ አድርጓል፡፡ በ2009 ዓ.ም. ኤኤዲ፣ በኤኤዲ መሪ ኢያድ አግ-ግሃሊ የሚመሩ ከአል-ቃዒዳ ጋር የዓላማ አንድነት ያላቸው ድርጅቶች ጥምረት ማለትም ጃማት ነስር አል-ኢዝላም ዋል ሙዝሊሚን (ጄኤንአይኤም)ን ተቀላቀለ፡፡
በመጋቢት 13 ቀን 2005 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንሳር አል-ዳይን (ኤኤዲ)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ቀደም ብሎ በመጋቢት 12 ቀን 2005 ዓ.ም. ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንሳር አል-ዳይን (ኤኤዲ) ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአንሳር አል-ዳይን (ኤኤዲ) ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአንሳር አል-ዳይን (ኤኤዲ) ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አንሳር አል-ዳይን (ኤኤዲ) ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
