ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ አብዱል ረዛ ሻሀላይ እና በሌላ መጠሪያው “ዩሱፍ አቡ አል-ካርክህ” እና ሀጂ ዩሱፍ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $15 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሻሀላይ በሰነዓ፣ የመን የሚገኘው የኢራን ኢስላማዊ አቢዮት ጥበቃ ኮር – ቆድስ ፎርስ (አይአርጂሲ-ኪውኤፍ) ከፍተኛ አዛዥ ነው፡፡ ሻሀላይ ለረዥም ጊዜ አሜሪካውያንን እና የዩናይትድ ስቴትስ ወዳጆችን በአለም ዙሪያ የጥቃት ኢላማ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ሻሀላይ በኢራቅ ከሚገኙ የጥምር ሀይሎች ጋር በርካታ ግንኙነቶችን አቅዷል፣ ለሽያ አክራሪ ቡድኖች የጦር መሳሪየ እና ፈንጂዎች አቅርቧል፣ በካርባላ፣ ኢራቅ፣ በጥር 1999 ዓ.ም. በተፈፀመው እና አምስት የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች የገደለው እና ሶስት ሌሎች ላይ የመቁሰል አደጋ ያስከተለውን ጥቃት አቅዷል፡፡
ከፍተኛ የአይአርጂሲ ሀላፊ እና ገንዘብ አቅራቢ እንደመሆኑ መጠን በ2003 ዓ.ም. ሻሀላይ በዋሽንግተን፣ ዲሲ ዩናይትድ ስቴትስ የሳውዲ አምባሳደርን ለመግደል የተዘጋጀውም እቅድ መርቷል፣ በገንዘብ ደግፏል፤ ይህ ግለሰብ በዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች አካባቢዎች ጥቃቶችን አቅዷል፡፡ ይህ እቅድ ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ በዩናይትድ ስቴትስ እስከ 200 ንጹሀን ዜጎች ይገደሉ ነበር፡፡
በመስከረም 30 ቀን 2004 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሻሀላይን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ ቀደም ሲል በ2000 ዓ.ም. የየገንዘብ ሚኒስቴር በኤክዘኪውቲቭ ኦርደር 13438 መሰረት ሻሀላይ በኢራቅ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም በኢራቅ መንግስት ላይ ስጋትን በመፍጠር በተመሳሳይ መልኩ መዝግቦት ነበር፡፡ በእነዚህ እርምጃዎች ምክንያት ሌሎችንም ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሻሀላይ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ሻሀላይ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አይአርጂሲ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ ይህ ግለሰብ በባህሬይን፣ በአውሮፓ ህብረት፣ በሳውዲ አረቢያ እና በዩናይትድ ኪንግደም በ2018 ሽብርተኛ ተብሏል፡፡
