ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ አብዱልራህማን ያሲን፣ በሌላ ስሙ አብዱል ራህማን ሰዒድ ያሲን እና አቦዉድ ያሲን ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ያሲን በየካቲት 1985 ዓ.ም. በኒው ዮርክ ከተማ በአለም አቀፍ የንግድ ማዕከል ላይ የተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ዋና እቅድ አውጪ የነበረው ራምዚ የሱፍ በቀጥታ እገዛ ሰጥቷል፡፡
በየካቲት 19 ቀን 1985 ዓ.ም. ያሲን ወደ አለም የንግድ ማዕከል ሙሉ ፈንጂዎች የጫነ ተሽከርካሪ ይዞ ከሄደው የሱፍ ጋር አብሮ ሄዷል፤ ይህንንም ተሽከርካሪ በንግድ ማዕከሉ የምድር በታች ማቆሚያ ውስጥ አቁመው ሄደዋል፡፡ ፈንጂዎቹ ሲፈነዱ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ 1000 ደግሞ ቆስለዋል፤ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ውድመት አስከትለዋል፡፡ ያሲን እንዳይታሰር ዩናይትድ ስቴትስን ለቆ ወደ ኢራቅ ተጉዟል፡፡ በዚህ ጥቃት ላይ ለነበረው ተሳትፎ ያሲን በዩናይትድ ስቴትስ በርካታ ክሶች እንዲመሰረቱበት ተብሏል፡፡
ያሲን በዩናይትድ ስቴትስ ተወልዶ በ1950ዎቹ ወደ ኢራቅ ተጓዘ፤ ከዚያም በ1984 ዓ.ም. ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተመለሰ፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ፓስፖርት አለው፤ በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ የሽብረተኞች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተካቷል፡፡
