ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ አብዱላህ ናውባሃር ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $2 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ናውባሃር ከኸዝብ-ኢ ኢዝላሚ ጉልቡዲን (ኤችአይጂ) ጋር ግነኙነት ያለው የፈንጂዎች ባለሙያ ሲሆን የአብዱል ሳቡር የጥቀት ኔትዎርክ የኤችአይጂ ቦንብ ሰሪ አባል ነው፡፡ ናውባሃር እና ሳቡር በመስከረም 08 ቀን 2005 ዓ.ም. በካቡል አለም አቀፍ አየር ማረፊያ፣ አፍጋኒስታን የውጭ አገር ሰራተኞችን ይዞ ይጓዘ በነበረ አውቶቡስ ላይ የተፈፀመወ የቦምብ ጥቃት ቁልፍ ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡
በመጋቢት 01 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ናውባሃርን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአልማግሪቢ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከናውባሃር ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡
