ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍተሕ ስለአብዱላሂ ኦስማን መሐመድ መረጃ ለሚሰጥ ሰው እስከ $5 ሚሊዮን ይከፍላል፡፡
መሐመድ በሌላ መጠሪያ ስሙ ኢንጂነር ኢስማኤል የሚባል ሲሆን፣ አልሸባብ በተባለው የሽብር ቡድን ውስጥ የፈንጂዎች ኤክስፐርት ነው፡፡ የአልሸባብን የፈንጂዎች ኦፕሬሽኖች እና ምርት በጠቅላላው የመምራት ኃላፊነት ያለበት ነው፡፡ እንዲሁም መሐመድ የአልሸባብ “ኢምር” ተብሎ ለሚታወቀው እና የአልሸባብ የሚዲያ ክንፍ አል-ካታኢብ መሪ ልዩ አማካሪ ሆኖ ያገለግላል፡፡
በኅዳር 08 ቀን 2013 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሐመድን ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በማለት በሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ ቁጥር 13224 በክፍል 1(ሀ)(ii)(ለ) መሠረት ሰይሞታል፡፡
