አብደልባሲጥ ሃምዛ ኤልሐሰን መሐመድ ኼይር

አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ሐማስ ተብሎ የሚታወቀውን ሽብርተኛ ድርጅት ወይም በሌላ ስሙ ሃረካት አል-ሙቃዋማ አል-ኢስላሚያ የፋይናንስ ማግኛ ዘዴዎችን ለማሰናከል የሚያስችል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

አብደልባሲጥ ሃምዛ ኤልሐሰን መሐመድ ኼይር በሱዳን የሚገኝ የሐማስ የፋይናንስ አቅራቢ ሲሆን፣ ከሐማስ የንግድ ድርጅቶች መካከል በርካቶቹን አስተዳድረዋል፡፡ ለረጅም ጊዜ ከአል-ቃዒዳ እና ከኦሳማ ቢን ላደን ጋር ግንኙነት ለነበራቸው ኩባንያዎች ለረጅም ጊዜ የፋይናንስ ግንኙነት ነበራቸው፡፡

ከዚህ ቀደም ለሐማስ ከሞላ ጎደል 20 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ በማስተላለፍ የተሳተፈ ሲሆን፣ በቀጥታ ለከፍተኛ የሐማስ የፋይናንስ ኦፊሰር እና በዩናትድ ስቴትስ ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ ተብሎ ለተሰየመው ማህር ጃዋድ የኑስ ሳላድ በቀጥታ ገንዘብ ልኳል፡፡

የሐምዛ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና ለሐማስ ገቢ የማስገኘት ኔትወርክ በሱዳን የሚገኘውን አል ሮውድ ሪል ኤስቴት ልማት፣ ዛውያ ግሩፕ ፎር ዲቨሎፕመንት ኤንድ ኢንቬስትመንት ኩባንያ ሊሚትድ እና ላሪኮም ፎር ኢንቬስትመንት ኩባንያን እንዲሁም በስፔን የሚንቀሳቀሰውን ዛውያ ግሩፕ ፎር ዲቨሎፕመንት ኢንቬስትመንት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅትን ያካተተ ነው፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር አራቱንም ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብረተኛ በማለት ሰይሟቸዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር በጥቅምት 07 ቀን 2016 ዓ.ም. በሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ (ኤግዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224፣ እንደተሻሻለው ሐምዛን ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በማለት ሰይሞታል፡፡ በዚህ መልኩ መሰየሙም የሽብር ጥቃት በሚፈጽሙ ወይም ከፍተኛ የመፈጸም ዕድል ያላቸውን የውጭ አገር ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች ላይ ዕግድ ይጥላል፡፡ ከዚህም ሌላ ይህ ትዕዛዝ የዩይነትድ ስቴትስ መንግሥት በዚህ ትዕዛዝ ስር ሽብርተኞች እና የሽብር ድርጅቶች ተብለው ለተሰየሙት ወይም ለእነርሱ የበታች ድርጅቶች፣ ሽፋን ሰጪዎች፣ ወኪሎች ወይም ተባባሪዎች ድጋፍ፣ አገልግሎቶች ወይም እገዛ የሚሰጡትን ግለሰቦች ወይም ተቋማት ንብረቶች እንዲያግድ የሚያዝ ነው፡፡

Skip to content