አል-ቃዒዳ (ኤኪው)

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

አል-ቃዒዳ የተደራጀው ሶቭየት ኅብረት አፍጋኒስታንን በወረረችበት ጊዜ ከአፍጋኒስታን ጎን ተሰልፈው ይዋጉ በነበሩ ዓረቦች፣ በኡሳማ ቢን ላዲን በ1980 ዓ.ም. ነበር፡፡ አል-ቃዒዳ በሙስሊሙ ዓለም የምዕራባዊያንን ተጽዕኖ ለማስወገድ፣ የእስላማዊ አገራት “ከሃዲ” መንግሥታትን ከስልጣን ማውረድ እና በራሱ የሸሪዓ ሕግ አተረጓጎም የሚገዙ ፓን-ኢስላማዊ ካሊፌቶችን ማቋቋም እና በመጨረሻም ይህ ሥርዓት አዲሱ ዓለም ዓቀፍ ሥርዓት እንዲሆን ይጥራል፡፡ ይህ ቡድን በ1988 ዓ.ም. በዩናይትድ ስቴትስ ላይ በይፋ ጦርነት ካወጀ ጊዜ ጀምሮ ይህ የድርጅቱ ዓላማ አልተቀየረም፡፡ በጸረ ሽብርተኝነት ጥረቶች አማካኝነት አል-ቃዒዳ በደርዘን የሚቆጠሩ መካከለኛ እና ከፍተኛ ደረጃ አባላቱን አጥቷል፤ አሁንም ግን ጥቃት ፈጻሚዎችን መመልመሉን፣ ጥቃቶችን ማቀዱን፣ ማነሳሳቱን እና መፈጸሙን አልተወም፡፡ አል-ቃዒዳ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአፍሪካ እና በእሲያ ተባባሪ ድርጅቶች አሉት፤ ዋነኛው ጥንካሬውም በእነዚህ ተባባሪ ድርጅቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

አል-ቃዒዳ (ኤኪው) በርካታ ሰዎች ለሞቱባቸው ጥቃቶች ኃላፊነት ይወስዳል፡፡ አል-ቃዒዳ በ1984 ዓ.ም. በኤደን፣ የመን በአሜሪካ ወታደሮች ላይ ሦስት የቦምብ ጥቃቶች ፈጽሟል፤ እንዲሁም በ1985 ዓ.ም. በሶማሊያ ለሄሊኮፕተሮች መውደቅ እና የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች መገደል ኃላፊነት ወስዷል፡፡ በተጨማሪም የ224 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፉት እና ከ5000 በላይ በሚሆኑት ላይ ደግሞ ጉዳት ያስከተሉት በናይሮቢ እና ዳር ኤ ሰላም የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዎች የቦምብ ጥቃቶች የእርሱ መሆናቸውንም ገልጾአል፡፡ በጥቅምት 1992 ዓ.ም. አል-ቃዒዳ ቦምብ በተጠመደባት ጀልባ በኤደን ወደብ በዩኤስኤስ ኮል ወታደራዊ መርከብ ላይ ጥቃት ፈጽሞ 17 የዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ኃይል ወታደሮች ሲገደሉ፣ ከ30 በላይ የሚሆኑት ቆስለዋል፡፡ በመስከረም 01 ቀን 1994 ዓ.ም. የአል-ቃዒዳ አባላት አራት የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ አውሮፕላኖችን በመጥለፍ እንዲከሰከሱ አድርገዋል ፡- ሁለቱ በኒው ዮርክ ከተማ የዓለም ንግድ ማዕከል፣ አንድ በፔንታጎን እና የመጨረሻው ደግሞ በሻንክስቪል፣ ፔንሲልቫኒያ መስክ ላይ፤ ይህ ጥቃት ከሞላ ጎደል 3000 ያህል ሰዎች ገድሏል፡፡

በመስከረም 27 ቀን 1992 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ቃዒዳን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ በመስከረም 13 ቀን 1994 ዓ.ም. አል-ቃዒዳ በሥራ አስፈጻሚ (ኤግዘኪውቲቭ) ትዕዛዝ 13224 አባሪ ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ቃዒዳ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ቃዒዳ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አል-ቃዒዳ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content