አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ (ኤኪውአይኤም)

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ቀደም ሲል ሳላፊስት ግሩፕ ለሰበካ እና ውጊያ (ጂኤስፒሲ) ይባል የነበረው ቡድን በ1998 ዓ.ም. አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ (ኤኪውአይኤም) ተብሎ ተመሰረተ፡፡ አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ በአብዛኛው በሻህል በክልል ላይ ትኩረት የሚያደርግ ቢሆንም፣ ይበልጥ ጸረ-ምዕራብ አለም ንግግር እና ርዕዮተ ዓለም ይዟል፡፡

አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶችን፣ ሲቪል ዒላማዎችን ዒላማ ማድረግ እና ለገንዘብ ሰዎችን ማገት እና ሌሎች የሽብር ተግባራትን ፈጽሟል፡፡ አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ በ1999 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ እና በአልጀርስ በአልጄሪያ የመንግሥት ሕንጻ ላይ የፈጸማቸው የቦንብ ጥቃቶች ለ60 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል፡፡ በጥር 2008 ዓ.ም. አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ በቡርኪናፋሶ በፈጸው ጥቃት ምክንያተ 28 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ 56 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በመጋቢት 2008 ዓ.ም. አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ በኮት ዲቯር የባሕር ዳርቻ መዝናኛ ላይ የፈጸመው ጥቃት ደግሞ ከ16 በላይ ሰዎች ሲገደል ሌሎች 33 ሰዎች ደግሞ አቁስሏል፡፡ በጥር 2009 ዓ.ም. አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብ በጋዎ፣ ማሊ ከ50 ሰዎች ላይ የገደለውን የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ፈጽሟል፡፡

በመጋቢት 18 ቀን 1994 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብን (ኤኪውአይኤም) በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ቀደም ብሎ በመስከረም 13 ቀን 1994 ዓ.ም. ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ቃዒዳ በኢስላማዊ ማግሪብን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የኤኪውአይኤም ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከኤኪውአይኤም ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ኤኪውአይኤም ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content