ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ አሊ ሰዒድ ቢን አሊ ኤል-ሁረይ በሌላ ስሙ አሊ ሰዒድ ቢን አል-ሀዎሪ ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ኤል-ሁረይ የሳውዲ ሂዝባላህ ሽብርተኛ ድርጅት አባል ነው የሚባል ሲሆን በ1988 በሳውዲ- አረቢያ በድሀራን መንትያ ህንፃዎች ላይ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ለነበረው ሚና ይፈለጋል፡፡
በሰኔ 18 ቀን 1988 ዓ.ም. የሳውዲ ሂዝባላህ አባላት በኮባር መንትያ ህንፃዎች (በዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ አባላት በመኖሪያነት ጥቅም ላይ የሚውል) የተሽከርካሪ ማቆሚያ በፕላስቲክ የተሰሩ ፈንጂዎች የያዘ ቦቴ ተሽከርካሪ ላይ የቦምብ ፍንዳታ ፈጽመዋል፡፡ በዚህ ፍንዳታ ምክንያት በአካባቢው የሚገኘውን ህንፃ አውድሞ 19 የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች እና አንድ የሳውዲ ዜጋ ሲሞቱ፣ የተለያዩ ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች ላይ መቁሰል አስከትሏል፡፡
በሰኔ 14 ቀን 1993 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ግራንድ ጁሪ አል-ሁረይ እና ሌሎች 13 ሌሎች ከጥቃቱ ጋር የተያያዙ ግለሰቦች እንዲከሰሱ ወስኗል፡፡
በጥቅምት 02 ቀን 1994 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ሁረይ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ሁረይ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ሁረይ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ ይህ ግለሰብ በኤፍቢአይ እጅግ የሚፈለጉ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፡፡
