ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ አህመድ ኢብራሀም አል-ሙግሀሲል በሌላ ስሙ አቡ ኦምራን ተብሎ ስለሚታወቀው ግለሰብ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-ሙግሀሲል የሳውዲ ሂዝባላህ የሽብር ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ መሪ መሆኑ ይገለፃል፤ ይህ ሰው በዳሃራን፣ ሳውዲ አረቢያ በሚገኙት መንትያ የኾባር ህንፃዎች ላይ በ1988 በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት ለነበረው ሚና ይፈለጋል፡፡
በሰኔ 18 ቀን 1988 ዓ.ም. የሳውዲ ሂዝባላህ አባላት በኮባር መንትያ ህንፃዎች (በዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ አባላት በመኖሪያነት ጥቅም ላይ የሚውል) የተሽከርካሪ ማቆሚያ በፕላስቲክ የተሰሩ ፈንጂዎች የያዘ ቦቴ ተሽከርካሪ ላይ የቦምብ ፍንዳታ ፈጽመዋል፡፡ በዚህ ፍንዳታ ምክንያት በአካባቢው የሚገኘውን ህንፃ አውድሞ 19 የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች እና አንድ የሳውዲ ዜጋ ሲሞቱ፣ የተለያዩ ዜግነት ባላቸው ግለሰቦች ላይ መቁሰል አስከትሏል፡፡
በሰኔ 14 ቀን 1993 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ግራንድ ጁሪ አል-ሙክሀሲል እና ሌሎች 13 ሌሎች ከጥቃቱ ጋር የተያያዙ ግለሰቦች እንዲከሰሱ ወስኗል፡፡
በጥቅምት 02 ቀን 1994 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አል-ሙክሀሲል አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚሀም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ሙክሀሲል ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ሙክሀሲል ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ ይህ ግለሰብ በኤፍቢአይ እጅግ የሚፈለጉ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል፡፡
