ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለዩናይትድ ስቴትስኤስ ኮል ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በጥቅምት 02 ቀን 1995 ዓ.ም. አጥፍቶ ጠፊዎች በዩናይትድ ስቴትስኤስ ኮል ላይ አነስተኛ፣ ፈንጂዎች የተጫኑበት ጀልባ በማምጣት አጋጭተዋል፤ ይህ መርከብ የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ሀይል ምሪት ያለው ሚሳኤል ዲስትሮየር ሲሆን በኤደን፣ የመን በሚገኝ ወደብ ጥቃቱ ተፈፅሟል፤ መርከቡ ነዳጅ ለመጫን ወደ ወደቡ ተጠግቶ ነበር፡፡ ይህንንም ተከትሎ የተከሰተው ፍንዳታ በመርከቡ የጎን ክፍል ላይ ሰፊ ቀዳዳ ከመፍጠሩም ሌላ 17 የመርከቡ ሰራተኞች ሞተው ከ30 በላይ የሚሆኑ ላይ ደግሞ ጉዳት ደርሷል፡፡ ይህ ጥቃት የታቀደው በአል-ቃዒዳ አባላት ነበር፤ከእነርሱም መካከል አሁን ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ጃማል አህመድ መሀመድ አሊ አል-በደዊ እና ፋሃድ መሀመድ አህመድ አል-ቁሶ ይገኙባቸዋል፡፡
