በአሳሴይ ሆቴል ላይ የተፈጸመ ጥቃት

አፍሪካ - ከሰሃራ በታች

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በ2011 ዓ.ም. በኪስማዮ፣ ሶማሊያ በሚገኘው አሳሴይ ሆቴል ላይ ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂ ስለሆነው መረጃ ለሚሰጥ ማንኛውም ሰው እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡

በሐምሌ 05 ቀን 2011 ዓ.ም. የአል-ሸባብ አጥፍቶ ጠፊ መግቢያ በር ባለው አሳሴይ ሆቴል ላይ ተደብቆ የነበረ የተመሳሰለ ፈንጂ አፈንድቶ ሌሎች አሸባሪዎች ወደ ሆቴሉ እንዲገቡ አስችሏቸዋል፡፡ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ሁለት አሜሪካዊያንን ጨምሮ 26 ሰዎች ሲገድሉ፣ በሌሎች 56 ሰዎች ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡

አል-ሸባብ በኬኒያ፣ ሶማሊያ እና ጎረቤት አገሮች ላይ በርካታ የሽብርተኛ ጥቃቶች በመፈጸም ተጠያቂ ድርጅት ሲሆን፣ በጥቃቶቹ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለሞት ተዳርገዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒቴር በመጋቢት 2000 ዓ.ም. አል-ሸባብን በውጭ አገር የሚገኝ የሽብር ድርጅት እና ልዩ ዓለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት ሰይሞታል፡፡ በሚያዝያ 2002 ዓ.ም. ደግሞ፣ አል-ሸባብ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የሶማሊያ የማዕቀብ ኮሚቴ በውሳኔ ቁጥር 1844 (2000) አንቀጽ 8 በዚሁ መልኩ ተሰይሟል፡፡

Skip to content