በዩናይትድ ስቴትስ ጊዜያዊ ሚሲዮን ተቋም እና በዩናይትድ ስቴትስ አኔክስ ላይ የተፈጸመ ጥቃት

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ በቤንጋዚ፣ ሊቢያ በዩናይትድ ስቴትስ ጊዜያዊ ሚሲዮን ተቋም እና በዩናይትድ ስቴትስ አኔክስ ላይ ስለተፈፀመው ጥቃት መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በመስከረም 01-02 ቀን 2005 ዓ.ም. አራት አሜሪካውያን ማለትም በሊቢያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ጆን ክርስቶፈር ስቴቨንስ፣ የውጭ አገልግሎት መረጃ ማኔጅመንት ኦፊሰር ሲን ስሚዝ እና የጥበቃ ስፔሻሊስቶች ግሌን አንተኒ ዶርቲ እና ታይሮን ስኖውደን ውድስ በዩናይትድ ስቴትስ ጊዜያዊ ሚሲዮን ተቋም እና በዩናይትድ ስቴትስ አኔክስ፣ ቤንዳዚ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ተገድለዋል፡፡ እነዚህ ሽብርተኞች ተቀጣጣይ፣ አውቶማቲክ የመሳሪያ እሳት፣ በሮኬት የሚተኮሱ ቦምቦች እና ሞተሮች በመጠቀም በሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ተቋማት እንዲሁም በሁለቱም ስፍራዎች መካከል በመጓጓዝ ላይ በነበሩ የዩናይትድ ስቴትስ ሰራተኞች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ጥቃቶች ሁለት ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ የቁስለት ጉዳት ሲያደርሱ፣ በሊቢያውያን ኮንትራት ጥበቃዎች ላይ ጉዳይ አስከትለዋል፤ ሁለቱም ፋሲሊቲዎች እንዲወድሙ እና እንዲተዉ አድርጓል፡፡

አምባሳደር ጆን ክሪስቶፈር ስቴቨንስ የ52 አመት እድሜ ያላቸው ነበሩ፤ በሰሜን ካሊፎርኒያ ተወልደው በ1991 በውጭ ጉዳይ አገልግሎት ስራ ጀመሩ፡፡ አምባሳደር ስቴቨንስ በበርካታ በውጭ አገራት ምድቦች የሰሩ ሲሆን በሊቢያ የሚሲዮኑ ዋና ሀላፊ በመሆን ከ1999-2001 ዓ.ም. ሰርተዋል፡፡ ከመጋቢት 2003 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 2003 ዓ.ም. አምባሳደር ስቴቨንስ የሊቢያ የሽግግር ብሄራዊ ምክር ቤት ልዩ ወኪል ሆነው አገልግለዋል፡፡ እንዲሁም በግንቦት 2004 ዓ.ም. በሊቢያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር በመሆን ትሪፖሊ ገብተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ አገልግሎት መስሪያ ቤት ውስጥ መስራት ከመጀመራቸው በፊት አምባሰደር ስቴቨንስ በዋሽንግተን ዲሲ የአለም አቀፍ ንግድ ጠበቃ ነበሩ፡፡ ቀደም ሲል ለሰላም ጓዶች በሞሮኮ ከ1975 -1977 ዓ.ም. የእንግሊዝኛ መምህር ሆነው አገልግለዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ሮድሀም ክሊንተን አምባሳደር ስቴቨንስ “ደፋር እና ጥሩ ሰው፣ ብቁ ዲፕሎማት እና የአሜሪካ ጀግና” ናቸው ብለዋል፡፡

ሲን ስሚዝ በሳን ዲዬጎ፣ ካሊፎርኒያ ተወለደ፤ በ1977 ዓ.ም. የአየር ሀይል አባል ሆኖ በግራውንድ ሬዲዮ ጥገና ስፔሻሊስት እና በሳጅንነት አገልግሏል፡፡ ስሚዝ በ2002 የውጭ ጉዳይ አገልግሎት ውስጥ በመረጃ ማኔጅመንት ኦፊሰርነት በተለያዩ ውጭ አገራት ለምሳሌ በባግዳድ፣ በፕሪቶሪያ፣ በሞንትሬል እና በሄግ ሰርቷል፡፡ ወደ ቤንጋዚ የተጓዘው በመስከረም 2004 ዓ.ም. ነበር፤ አላማውም ለዩናይትድ ስቴትስ ጊዜያው ሚሲዮን ተቋም የቴሌኮሙኒኬሽን እና የአመራር ድጋፍ ለመስጠት ነበር፡፡

ግሌን አንተኒ ዶርቲ የ42 አመት እድሜ የነበረው የኔቪ ሲል አባል ነበረ፤ የተወለደው ዊንቸስተር፣ ማሳቹሴትስ ሲሆን ኔቪውን የተቀላቀለው በ1987 ዓ.ም. ነበር፡፡ በኢራቅ እና በአፍጋኒስታን በዚህ ሙያ አገልግሏል፡፡ የባህር ሀይል አባል ከመሆኑ በፊት ዶርቲ የበረዶ መንሸራተት አሰልጣኝ ሆኖ ሰርቷል፤ የበረራ ት/ቤት ገብቶ ተምሯል፡፡ የፓራሜዲክ እና የበረራ አሰልጣኝ ነበር፡፡ በ1997 ዓ.ም. ዶርቲ በውጭ አገር የሚገኙ ባለስልጣኖች ጥበቃ በማድረግ በኮንትራት ይሰራ ነበር፡፡ ዶርቲ ወደ ቤንጋዚ የተጓዘው በመስከረም 2004 ዓ.ም. ሲሆን ለዩናይትድ ስቴትስ ሰራተኞች ጥበቃ ያደርግ ነበር፡፡

ታይሮን ስኖውደን ውድስ፣ እድሜ 41፣ በፖርትላንድ፣ ኦሪገን ተወለደ፤ ለ20 አመታት በኔቪሲልነት አገልግሏል፡፡ በሶማሊያ፣ ኢራቅ እና አፍጋኒስታን በተለያዩ ጊዜዎች ሰርቷል፡፡ ውድስ የተመዘገበ ነርስ እና የምስክር ወረቀት ያለው ፓራሜዲክ ነበር፡፡ በ2002 ዓ.ም. ውድስ በኮንትራት የጥበቃ ኦፊሰርነት በመስራት በውጭ አገር ለሚገኙ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጥበቃ ያደርግ ነበር፡፡ በአለም ዙሪያ ለሀላፊዎች ጥበቃ በማድረግ ሰርቷል፡፡ ውድስ ወደ ቤንጋዚ የተጓዘው በመስከረም 2004 ዓ.ም. ለዩናይትድ ስቴትስ ሰራተኞች ጥበቃ ለማድረግ ነበር፡፡

Skip to content