ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በታኅሳስ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በማንዳ ቤይ የአውሮፕላን መስክ ላይ ለደረሰው የሽብር ጥቃት ስለ ማሊም አይመን እና ስለማንኛውም ሌላ ለጥቃቱ ተጠያቂ ስለሆነ ሰው መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ወሮታ ይከፍላል፡፡ በኬኒያ የሚገኘው ማንዳ ቤይ የአውሮፕላን መስክ የናይትድ ሰቴትስ የምሥራቅ አፍሪካ አጋሮቿ ለሽብር ቀውስ ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ እና በክልሉ የአሜሪካን ጥቅሞች ለማስጠበቅ ሥልጠና ለመስጠት እና ለጸረ- ሽበር ድጋፍ የምትጠቀምበት ስፍራ ነው፡፡
ጸሐይ ከመውጧቷ በፊት የአል-ሸባብ ታጣቂዎች በጦር ሰፈሩ ውስጥ በኬኒያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ይዞታዎች ላይ የሞርታር ጥቃት ከፈቱ፤ በተመሳሳይም ጊዜ አጎራባች በሆነው የአውሮፕላን መስክ ላይ በሮኬት የሚወነጨፉ ፈንጂዎች (RPG) እና ቀላል ጥይቶች ተኮሱ፡፡ ሁለት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የዲኦዲ የኮንትራት ፓይለቶች ወታደራዊ አውሮፕላኖቻቸው በማቆሚያው ስፍራ በሮኬት የሚወነጨፉ ፈንጂዎች በመመታታቸው ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ሦስተኛ የዲኦዲ የኮንትራት ሠራተኛ የነበረ የአሜሪካ ዜጋ ከፍንዳታው በሕይወት ቢተርፍም እንኳን ከፍተኛ ቁስለት ደርሶበታል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል ስፔሻሊስት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሆኖ በመሥራት ላይ ሳለ በቀጠለው ውጊያ ሲገደል ሁለት ሌሎች የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ወታደሮች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
የአልሸባብ ኃላፊ የሆነ ሰው ለሻሃዳ የዜና ኤጀንሲ ከጊዜ በኋላ በለቀቀው ቪድዮ የቡድኑ ቃል አቀባይ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን የሚወስደው አል-ሸባብ መሆኑን ገልጾአል፡፡
ማሊም አይመን በኬኒያ እና ሶማሊያ የሽብር ጥቃቶችን የሚፈጽመው፣ የአልሸባብ ዩኒት የሆነው ጃይሽ አይመን መሪ ሲሆን፣ በኬኒያ እና ሶማሊያ በጥር 2012 ዓ.ም. ለተፈጸመው ጥቃት ተጠያቂ ነው፡፡ በኅዳር 2012 ዓ.ም.፣ የዩናይትድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አይማንን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ (SDGT) በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡
አል-ሸባብ የአል-ቃዒዳ የምሥራቅ አፍሪካ ዋነኛ ተባባሪ ድርጅት ሲሆን ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችን ጨምሮ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑ ጥቃቶችን በኬኒያ፣ ሶማሊያ እና በአጎራባች አገራት ፈጽሟል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒቴር በመጋቢት 2000 ዓ.ም. አል ሸባብን የውጭ አገር የሽብር ድርጅት (FTO) እና ልዩ ዓለም ዓቀፍ የሽብር ድርጅት ብሎታል፡፡ በሚያዝያ 2002 ዓ.ም. ፣ አል-ሸባብን ልዩ ዓለም ዓቀፍ ድርጅት በማለት ሰይሞታል፡፡ በሚያዝያ 2002 ዓ.ም. አል-ሸባብ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት የማዕቀብ ኮሚቴ ውሰኔ ቁጥር 1844 (2008) መሠረት የሽብርተኝነት ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
