ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ አይሲስ-ዲአርሲ መሪ ሙሳ ባሉኩ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡
በሴካ ሙሳ ባሉኩ አመራር ስር አይሲስ-ዲአርሲ ሰዎችን ዒላማ ያደርጋል፣ ይገድላል፣ ገጽታ ይቀይራል እንዲሁም ሌሎች ወሲባዊ ጥቃቶች ይፈጽማል፣ ሕጻናትን ጨምሮ ዜጎችን ይጠልፋል፡፡ ይህ ቡድን በዲአርሲ በንቲ ግዛት ውስጥ ጥቃቶች እና የጉልበት ብዝባን ለመፈጸም ሕጻናትን ይጠቀማል፡፡ አይሲስ-ዲአርሲ በሌላ መጠሪያ ስሙ አላይድ ዴሞክራቲክ ፎርስስ (ኤዲኤፍ) እና ማዲና አት ታውሂድ ዋዉ ሙጃሂዲን ተብሎ ይታወቃል፤ ሌሎችም ስሞች አሉት፡፡ ይህ ቡድን በምሥራቃዊ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ በጎንጎ ዜጎች እና በክልላዊ ወታደራዊ አካላት ላይ እጅግ ጭካኔ የሞላበት ጥቃት ፈጽሟል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት መሠረት ይህ ቡድን በ2020 ብቻ ከ849 በላይ ሰዎች ገድሏል፡፡
በመጋቢት 2013 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባላኩን ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ (SDGT) በማለት መዝግቦታል፡፡ በተመሳሳይ ጊዜ፣ ሚኒስቴሩ አይሲስ-ዲአርሲን በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት እና ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በማለት መዝግቦታል፡፡
በእነዚህ ስያሜዎች ምክንያት፣ ከሌሎች ውጤቶችም እንደተጠበቁ ሆነው፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሥልጣን ወሰን ውስጥ የሚገኙ፣ ከላይ የተገለጹት ስያሜዎች የተሰጣቸው አካላት ንብረቶች ታግደዋል፤ በዩናይትድ ስቴትስ ሰዎችም በጠቅላላው ከእነርሱ ጋር ምንም ዓይነት ልውውጥ እንዳያደርጉ ተከልክለዋል፡፡ በውጭ አገር የሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ስለ ባሉኩ ወይም አይሲስ-ዲአርሲ ከፍተኛ ልውውጥ ያደረጉ እንደሆነ በዩናይትስ ስቴትስ ተያያዥ ሂሳብ ወይም በሒሳብ ለሚከፈሉ ክፍያዎች የሚጣል ዕግድ ሊጣልባቸው ይችላል፡፡ በተጨማሪም ሆን ብሎ ለአይሲስ-ዲአርሲ የማቴሪያል ወይም የኃብቶች እገዛ ማድረግ ወይም እንዲህ ያለውን ድጋፍ ለማድረግ መሞከር ወይም መመሳጠር ወንጀል ነው፡፡
ኤዲኤፍ ቀደም ሲል በ2006 ዓ.ም. በፈጸማቸው የኃይል ድርጊቶች እና ጭካኔዎች ምክንያት በዩናይትድ ስቴትስ የገንዘበ ሚኒስቴር ማዕቀብ ተጥሎበት ነበር፡፡ የየናትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሉኩ እና ሌሎች አምስት ኤዲኤፍ አባላት በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ በነበራቸው ሚና ምክንያት በ2011 ዓ.ም. በግሎባል ማግኒትስኪ የማዕቀብ ፕሮግራም መሠረት እቀባ ተጥሎባቸዋል፡፡ በ2012 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት በዲአርሲ ፕሮግራም ማዕቀቦች ስር ባሎኩን ለተጨማሪ ማዕቀቦች ፈርጆታል፡፡
