ሳጂድ ሚር

ደቡብ እና መካከለኛው እስያ

ወሮታ

እስከ 5 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሳጂድ ሚር በሌላ ስሙ ሳጂድ ማጂድ ቹህድሪ እና ሳጂድ ማጂድ መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ሚር ላሽካር-ኢ-ጣይባ (ኤልኢቲ) የተባለው የፓኪስታን በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት (ኤፍቲኦ) ከፍተኛ አባል ሲሆን፣ ይህ ግለሰብ በኅዳር 2001 ዓ.ም. በሙምባይ ለተፈጸመው ጥቃት ተፈላጊ ነው፡፡ ሚር የኤልኢቲ የኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ በመሆን በጥቃቶቹ ዕቅድ አወጣጥ፣ ዝግጅት እና አፈጻጸም ላይ የመሪነት ሚና ተጫውቷል፡፡

ከኅዳር 17 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ኅዳር 20 ቀን 2001 ዓ.ም. ድረስ በኤልኢቲ የሰለጠኑ 10 ግለሰቦች በሙምባይ፣ ሕንድ ተከታታይ የተቀናጀ ጥቃት በመፈጸም 166 ሰዎች ገድለዋል፡፡ በ3 ቀናቱ ከበባ ከተገደሉት መካከል ስድስቱ አሜሪካዊያን ነበሩ፡፡ እነርሱም፡- ቤን ዚዮን ክሮማን፣ ጋቭሪየል ሆልትዝበርግ፣ ሳንዲፕ ጄስዋኒ፣ አለን ሼር፣ ናኦሚ ሼር እና አርያህ ሌይቢሽ ቴይቴልባውም ናቸው፡፡

ሚር መግምት ከ1994 ዓ.ም. ጀምሮ የኤልኢቲ አባል ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከ1998 ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም. ድረስ፣ ሚር የኤልኢቲ ውጫዊ ኦፕሬሽኖች ኃላፊ ነበር፤ ለቡድኑም ልዩ ልዩ ጥቃቶችን አቅዷል፣ መርቷል፡፡ በተጨማሪም ሚር ከ2000 ዓ.ም. እስከ 2001 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በዴንማርክ በአንድ ጋዜጣ ድርጅት እና በሠራተኞቹ ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተመሳጥሯል ተብሏል፡፡

ሚር በሙምባይ ጥቃቶች ላይ ለነበረው ተሳትፎ በሚያዝያ 2003 ዓ.ም. በዩናይትድ ስቴትስ የቀረበበትን ክስ ይከላከል የሚል ብይን ተሰጥቶበታል፡፡ በነሐሴ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚርን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሚር ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሚር ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ኤልኢቲ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡ ሚር በኤፍቢአይ እጅግ ተፈላጊ ሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ተካቷል፡፡

Skip to content