ሳይፍ አል-አዲል

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 10 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሳይፍ አል-አዲል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አል-አዲል በኢራን የሚገኘው የአል-ቃዒዳ ከፍተኛ መሪ እንዲሁም መጅሊስ አል-ሹራ ተብሎ የሚጠራው የአል-ቃዒዳ ከፍተኛ የአመራር ምክር ቤት አባል ነው፡፡ አል-አዲል የአል-ቃዒዳን ወታደራዊ ኮሚቴ ይመራል፡፡

አል-አዲል በዳር ኤስ ሰላም፣ ታንዛኒያ እና በናይሮቢ፣ ኬንያ በዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዎች ላይ በተፈጸሙት ጥቃቶች ለነበራቸው ሚና በዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ግራንድ ጁሪ በኅዳር 1990 ዓ.ም. ክስ እንዲቀርብባቸው ተወስኖ፣ ተከስሰዋል፡፡ በእነዚህ ጥቃቶች 224 ንጹሃን ሲሞቱ፣ ከ5000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል፡፡

ከ1990 ዓ.ም. የአሜሪካ ኤምባሲ የቦንብ ጥቃቶች በኋላ አል-አዲል ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢራን በመዘዋወር በኢራን አቢዮት ጥበቃ ሠራዊት ሽፋን ተሰጥቶት ኖሯል፡፡ በሚያዝያ 1995 ዓ.ም. የኢራን ባለሥልጣናት እርሱን እና ሌሎች የአል-ቃዒዳ መሪዎች በቁም እስር እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡

በመስከረም 2007 ዓ.ም. አል-አዲል እና አራት ከፍተኛ የአል-ቃዒዳ አመራሮች በየመን በአል-ቃዒዳ በታገቱት የኢራን ዲፕሎማት ፈንታ በኢራን ተፈትተዋል፡፡

አል-አዳል በኢራን የአል-ቃዒዳ መስራች አል-ዛርቃዊ ከፍተኛ አመራር ነበር፤ ይህ ቡድን በኋላ የኢራቅ እና ሶሪያ ኢስላማዊ መንግሥት (አይሲስ) ሆኗል፡፡

በ1982 ዓ.ም. አል-አድል እና ሌሎች የአል-ቃዒዳ አባላት እንደ አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን እና ሱዳን ባሉ አገራት ወታደራዊ እና የስለላ ሥልጠናዎችን ለአል-ቃዒዳ እና እንደ የግብጹ ኢስላሚክ ጅሃድ ላሉ የአል-ቃዒዳ ተባባሪ ድርጅቶች ሰጥቷል፡፡

ከ1984 ዓ.ም. እስከ 1985 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ለአል-ቀዒዳ አባላት እና በኦፕሬሽን ሪስቶር ሆፕ ወቅት በሞቃዲሹ ከዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች ጋር ለተዋጉት የሶማሌ ጎሳዎች ወታደራዊ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በ1970ዎቹ አጋማሽ አካባቢ የግብጽ ልዩ ኃይል ሌ/ኮሎኔል የነበረ እንደመሆኑ መጠን የግብጽን መንግሥት ለመገልበጥ በተደረጉት ሙከራዎች ውስጥ ተሳትፏል፡፡ በ1979 ዓ.ም. በግበጽ የአገር ውስጥ ሚኒስትር ላይ የግድያ ሙከራ ከተደረገ በኋላ በሺዎች ከመቆጠሩ ታጣቂ የመንግሥት ተቃዋሚዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ከእስር ሲፈታ አል-አድል ማዕረጉ ተገፈፈ፤ በ1981 ዓ.ም. ወደ አፍጋኒስታን ተጉዞ የአል-ቃዒዳ አሰልጣኝ ሆነ፡፡

በመስከረም 13 ቀን 1994 ዓ.ም. አል-አድል በሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 አባሪ ውስጥ ተጠቅሷል በዚህም ትዕዛዝ ስር ልዩ ዓለም ዓቀፍ ሽብርተኛ በሚል ማዕቀብ ይጣልበታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የአል-ጃቡሪ ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከአል-ጃቡሪ ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው አል-ቃዒዳ ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content