ስለ ተቋሙ
ሳውዲ ሂዝባላህ በ1970ዎቹ የተመሠረተ፣ በአሜሪካዊያን እና በሳውዲ ዓረቢያ በሚገኙ የአሜሪካ ንብረቶች ላይ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ የሚቀሰቅስ ድርጅት ነው፡፡ ይህ ድርጅት በ1988 ዓ.ም. በዳሃራን፣ ሳውዲ ዓረቢያ በኾባር ሕንጻዎች ላይ የቦምብ ጥቃት ፈጽሟል፡፡ ይህ ጥቃት 19 የአሜሪካ ወታደሮችን እና አንድ የሳውዲ ዜጋ ሲገደል፣ የልዩ ልዩ አገራት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ደግሞ አቁስሏል፡፡
