ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ ስለ ሳሊም ጀማል አያሽ በሌላ ስሙ ጃሊል አያሽ እና ጃበር መረጃ ለሚሰጥ እስከ $10 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ አያሽ የሽብርተኛው ሂዝባላ መቺ ስኳድ ዩኒት 121 ከፍተኛ አባል ነው፤ ይህ ዩኒት ትዕዛዝ የሚሰጠው በቀጥታ ከሂዝባላህ ዋና ጸሐፊ ሃሰን ናስረላህ ነው፡፡ አያሽ በዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ላይ ጉዳት ለማድረስ በተደረጉ ጥረቶች መሳተፉ ይታወቃል፡፡
በነሐሴ 11 ቀን 2020 ዓ.ም. ዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት የሊባኖስን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራፊክ ሃሪሪ ሕይወት በቀጠፈው በመኪና ላይ ከተጠመደ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ በቀረበበት የሽበር ክስ አያሽን በሌለበት አምስት የእድሜ ይፍታህ እስሮች ፈርዶበታል፡፡ እንዲሁም ይህ ጥቃት ሌሎች 21 ሰዎችን ሲገድል፣ 226 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የራፊክ ሃሪሪን ሕይወት የቀጠፈውን ጥቃት የፈጸመው ቡድን የተመራው በአያሽ ነበር፤ ስለሆነም ፍርድ ቤቱ አያሽ በዚያ ዕለት በተፈጸመው ግድያ ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበረው ብሏል፡፡
