ራዱላን ሳህሪዮን

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

እስከ 1 ሚሊዮን ዶላር

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ወሮታ ለፍትሕ ስለ ራዱላን ሳሂሮን፣ በሌላ ስሙ ኮማንደር ፑቶል መረጃ ለሚሰጥ እስከ $1 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ ከ1997 ዓ.ም. ሳሂሮን በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት (ኤፍቲኦ) ተብሎ የተሰየመው፣ በፊሊፒንስ የሚገኘው አቡ ሳያፍ ቡድን (ኤኤስጂ) አጠቃላይ መሪ ነው፡፡

ሳሂሮን የአሜሪካ እና የሌሎች አገራት ዜጎች ተጠቂዎች የሆኑባቸው በርካታ የቦንብ ጥቃቶች እና እገታዎች ፈጽሟል፡፡

ሳሂሮን በ1996 ዓ.ም. በጆሎ ደሴት የቦንብ ጥቃት እንዲፈጸም ትዕዛዝ ሰጥቶ 11 የፊሊፒንስ ዜጎች እና አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደር ሞተዋል፣ ከ200 በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡ በፍንዳታው ጥቅም ላይ የዋለው ድብቅ ቦምብ የተገጣጠመው በሳሂሮን ዋና ቦታ በካምፕ ቲቢግ ቱህ-ቱህ፣ ጆሎ ደሴት፣ ፊሊፒንስ ነበር፡፡ ሳሂሮን በግንቦት 1993 ዓ.ም. በፓላዋን፣ ፊሊፒንስ የቱርስት መዝናኛ በተፈጸመው የሦስት የአሜሪካ ዜጎች እና የ17 ፊሊፒንስ ዜጎች እገታ የራሱን ሚና ተጫውቷል፡፡ አሜሪካዊውን ጉዊሌርሞ ሶቤሮን ጨምሮ በርካቶቹ ታጋቾች ተገድለዋል፡፡ ሳሂሮን በሚያዝያ 1992 ዓ.ም. በሲፓዳን፣ ማሌዢያ በሚገኘው መዝናኛ የተፈጸመው እገታ ቁልፍ መሪ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ ሳሂሮን እና አራት ሌሎች የኤኤስጂ አባላት ምዕራባዊያንን፣ የማሌዢያ እና የፊሊፒንስ ዜጎችን ጨምሮ 21 የውጭ አገር ዜግነት ያላቸውን ቱሪስቶች እና የመዝናኛውን ሠራተኞች አግተው ወሰዱ፡፡

ሳሂሮን በኤኤስጂ ውስጥ በርካታ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ይዟል፡፡ ከ1991 ዓ.ም. ጀምሮ የኤኤስጂ መጅሊስ ሹራ (አማካሪ ምክር ቤት) አባል ሆኖ ቆይቷል፡፡ በ1994 ዓ.ም. አጋማሽ የኤኤስጂ መሪ የኻዳፋይ ጃንጃላኒ አማካሪ ሆኖ አገልግሏል፡፡ በተጨማሪም ሳሂሮን በደቡብ ፊሊፒንስ የሱሉ አርኪፔላጎ ተዋጊዎች ልዩ ልዩ የአመራር ቦታዎችን ይዞ ቆይቷል፡፡ ከ1992 ዓ.ም. እስከ 1995 ዓ.ም. ሳሂሮን በደቡብ ፊሊፒንስ ሱሉ በጆሎ ደሴት አካባቢ የሚንቀሳቀሰው በግምት 100 አባላት ያሉት ፑቶል ተብሎ የሚጠራው የኤኤስጂ ቡድን መሪነትን ጨምሮ በኤኤስጂ በርካታ የመሪነት ኃላፊነቶች ሚናዎች ነበሩት፡፡ በሱሉ የሚገኘው 18 ታጣቂ ቡድኖች ያሉት ኤኤስጂ መሪ፤ በሱሉ የኤኤስጂ ኤታማዦር ሹም እና በግምት 1000 ባለ ሙሉ ትጥቅ ተከታዮች ያሉት የጆሎ የኤኤስጂ አጠቃላይ መሪ ሆኖ አገልግሏል፡፡

ሳሂሮን ሚንዳናኦ ወይም ፓቲኩል ጆሎ፣ ሱሉ፣ ፊሊፒንስ ተደብቆ ሳይኖር አይቀርም፡፡

በየካቲት 20 ቀን 1999 ዓ.ም. ሳሂሮን በዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ፍርድ ቤት ክስ ይቅረብበት የሚል ብይን ተሰጥቶበት በእገታ ክስ ቀርቦበታል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በተመሳሰይ ቀን የእስር ትዕዛዝ አውጥተውበታል፤ ሳሂሮን በዩናይትድ ስቴትስ እጅግ ተፈላጊ ሽብርተኞች ዝርዝር ተካቷል፡፡

በኅዳር 21 ቀን 1998 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር ሳሂሮንን ልዩ አለምአቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት ሌሎች እርምጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሳሂሮን ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሳሂሮን ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ኤኤስጂ ድርጅት ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡

Skip to content