ስለ ተቋሙ
ወሮታ ለፍትሕ በ1995 ዓ.ም. በሳውዲ ዋና ከተማ በመኖሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ስለተፈጸሙ የቦምብ ጥቃቶች መረጃ ለሚሰጥ እስከ $5 ሚሊዮን ወሮታ ይከፍላል፡፡ በግንቦት 04 ቀን 1995 ዓ.ም. ቢያንስ 15 ጥቃት ፈጻሚዎች በሳውዲ ዓረቢያ ሪያድ ከተማ ዳርቻ በሚገኙ ሦስት የመኖሪያ ቅጥር ግቢዎች ላይ ጥቃት ፈጸሙ፡፡ የጥበቃ ሠራተኞችን ካለፉ በኋላ ጥቃት ፈጻሚዎቹ በቅጥር ግቢዎቹ ውስጥ በመኪና ላይ የተገጠሙ ቦምቦች በማፈንዳት ዘጠኝ አሜሪካዊያንን ጨምሮ 35 ሰዎች ተገድለዋል፤ 200 ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ የጥቃቱ ዒላማ የተደረጉ ግቢዎች በርካታ የምዕራቡ ዓለም በተለይም የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ዜጎች የሚኖሩባቸው ነበሩ፡፡ የዚህ ጥቃት አደራጅ እና አስተባባሪ አል-ቃዒዳ ነበር፡፡
