ሪቮሉሽነሪ ኦርጋናይዜሽን 17 ኖቬምበር (17ኤን)

አውሮፓ እና ዩራሺያ

ወሮታ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

ሪቮሉሽነሪ ኦረጋናይዜሽን 17 ኖቬምበር (17ኤን) የተመሠረተው በ1967 ዓ.ም. አክራሪ ግራ ዘመም ድርጅት ሆኖ ነበር፡፡ ይህ ቡድን የአሜሪካን የጦር ሰፈር ከግሪክ ለማንሳት፣ ከሳይፕረስ የቱርክን ወታደራዊ ኃይል ለማስወገድ እንዲሁም ግሪክ ከኔቶ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማቋረጥ ፍላጎት ነበረው፡፡ 17ኤን በግሪክ ውስጥ ለተፈጸሙ በርካታ የሽብር ተግባራት ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡ ከእነርሱም መካከል፡- ተኩሶች፣ የሮኬት ጥቃቶች እና በተሽከርካሪ የተጠመዱ ቦምቦች ይካተታሉ፡፡ በዚህ ቡድን የሽብር እንቅስቃሴዎች ምክንያት አራት አሜሪካዊያን ሞተዋል፤ እነርሱም፡- ዊሊያም ኖርዲን፣ ሮናልድ ስቴዋርት፣ ጆርጅ ጻንቴስ እና ሪቻርድ ዌልሽ ይገኙባቸዋል፡፡ የ17ኤን አንድ አካል በአቴንስ የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ለተፈጸመው በሮኬት ማስወንጨፊያ የታገዘ የቦምብ ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል፡፡

በመስከረም 28 ቀን 1990 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 17ኤንን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ከነሐሴ 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የ17ኤንን በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ምዝገባን ሰርዟል፡፡

Skip to content