ስለ ተቋሙ
ሪቮሉሽነሪ ስትራግል (አርኤስ) የተመሠረተው የሌሎች ሁለት የግሪክ ማርክሲስት ቡድኖች ማትም 17 ኖቬምበር እና ሪቮሉሽነሪ ፒፕልስ ስትራግል አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ በ1995 ዓ.ም. ነበር፡፡ ይህ አክራሪ ማርክሲስት ቡድን በግሪክ እና በግሪክ ውስጥ በሚገኙ የአሜሪካ ዒላማዎች ላይ ጥቃት ፈጽሟል፡፡ ሪቮሉሽነሪ ስትራግል ታዋቂነት ያተረፈው በነሐሴ 30 ቀን 1995 ዓ.ም. የ17 ኖቬምበር አበላት በፍርድ ሂደት ላይ ሳሉ በአቴንስ በሚገኝ ፍርድ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት ባደረሰ ጊዜ ነበር፡፡ ሪቮሉሽነሪ ስትራግል በአቴንስ በጥር 1999 ዓ.ም. በአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ለተፈጸመው በሮኬት ማስወንጨፊያ የታገዘ የቦምብ ጥቃት እንዲሁም በመጋቢት 2001 ዓ.ም. በአቴንስ በሲቲ ባንክ ቅርንጫፍ ላይ ለተፈመው የቦምብ ጥቃት ኃላፊነት ወስዷል፡፡
በግንቦት 10 ቀን 2001 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪቮሉሽነሪ ስትራግል (አርኤስ)ን በተሻሻለው የኢምግሬሽን እና ዜግነት ሕግ፣ በክፍል 219 መሠረት በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፡፡ ቆየት ብሎ በመስከረም 07 ቀን 2002 ዓ.ም. የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪቮሉሽነሪ ስትራግልን ልዩ አለም አቀፍ ሽብርተኛ በማለት በስራ አስፈፃሚ ትእዛዝ (ኤክዘኪውቲቭ ኦርደር) 13224 እንደተሻሻለው መዝግቦታል፡፡ በዚህም መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ወሰን ውስጥ የሚገኙ የሪቮሉሽነሪ ስትራግል ንብረቶች እና ጥቅሞች ሁሉ ታግደዋል፣ ማናቸውም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ከሪቮሉሽነሪ ስትራግል ጋር በምንም አይነት ልውውጥ ላይ መሳተፍ አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትስ በውጭ አገር የሚገኝ ሽብርተኛ ድርጅት በሚል ለተመዘገበው ሪቮሉሽነሪ ስትራግል ሆን ብሎ የማቴሪያል ወይም የሀብቶች አቅርቦት ማድረግ፣ ወይም ለማቅረብ መመሳጠር የተከለከለ ወንጀል ነው፡፡
