ሞሮ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት (ኤምኤንኤልኤፍ)

ምስራቅ አቅራቢያ - ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ

ወሮታ

የበኩልዎን ያድርጉ

ስለ ተቋሙ

የሞሮ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት (ኤምኤንኤልኤፍ) በ1964 ዓ.ም. በፊሊፒንስ ተመሰረተ፡፡ የዚህ ድርጅት አጀማመርም ከሙስሊም ኢንዲፔንደንስ ሙፍመንት አንጃ ሆኖ የተመሠረተ ነው፡፡ የሞሮ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት ከ1960ዎቹ ጀምሮ ለሁለት አስርተ ዓመታት ያህል ጊዜ ከሞሮ ተገንጣይ ቡድኖች መካከል ዋነኛው ድርጅት ነበር፤ በርካታ የሞሮ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት አባላት ይህንን ድርጅት ለቅቀው ወጥተው በፊሊፒንስ እጅግ የኃይል ድርጊት ፈጻሚ የሆነውን አቡ ሳይፍ ግሩፕ (ኤኤስጂ) በመባል የሚታወቀውን መሠረቱ፡፡

በ1988 ዓ.ም. የሞሮ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት ከፊሊፒን መንግሥት ጋር ስምምነት በመፈረም ልዩ የሰላም እና ልማት ዞን (ኤስዜድኦፒኤዲ) አቋቋሙ፡፡ የሞሮ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት ሊቀመንበር ኑር ሚሱአሪ ሁለት የዋናው የፊሊፒን ክፍለ አገራትን እና በዋናነት ሙስሊሞች የሚኖሩባቸውን ሦስት ደሴቶች ያካተተው የሙስሊም ሚንዳናዎ የራስ ገዝ (ኤአርኤምኤም) አስተዳዳሪ ሆኖ ተሾመ፡፡ ይህም ግዛት በተወሰነ ደረጃ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ተሰጠው፡፡ ሚንዳናዎ ውስጥ በአክራሪ አማጺያን እና በመንግሥት መካከል ግጭቶች መከሰታቸው ቀጠለ፤ በርካቶች የክልሉ ነዋሪዎችም ትርጉም ላለው የራስ ገዝ አስተዳደር እና ልማት ሊያሰራ የሚችል ፍሬምወርክ እንዲፈጠር ጠይቀዋል፡፡

በመስከረም 19 ቀን 2002 ዓ.ም. የሞሮ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት የጠመደው ፈንጂ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን አፈንድቷል፡፡ በዚህ ፍንዳታ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይል ወታደሮች እና የፊሊፒንስ የጦር ኃይል (ኤኤፍፒ) አንድ ወታደር ተገድለዋል፤ እነዚህ ወታደሮች በዚህ አካባቢ ትምህርት ቤት ለመገንባት በሰብዓዊ ሥራ ላይ ተሰማርተው ነበር፡፡

በ2005 ዓ.ም. የሞሮ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት ስርዓት አልበኛ አባላት ዛምቦአንጋ ከተማ ላይ ለሦስት ሣምንታት የቆየ የኃይል ድርጊት ፈጽመው በደርዘን የሚቆጠሩ የፊሊፒንስ የጸጥታ ኃይል አባላትን ሲገድሉ በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ተፈናቅለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የሞሮ ናሽናል ሊብሬሽን ፍሮንት በርካታ አንጃዎች አሉት፤ አንዳንዶቹ ከፊሊፒንስ መንግሥት እና ከአንጃው ሞሮ ኢስላሚክ ሊበሬሽን ፍሮንት ጋር የሚደረጉ ድርድሮችን የሚደግፉ ናቸው፡፡ እነዚህ ድርድሮች በ2010 ዓ.ም. የባንግሳሞሮ ኦርጋኒክ ሕግ (ቢኦኤል) እንዲጸደቅ እና ባንግሳሞሮ የሙስሊም ሚናዳናዎ የራስ ገዝ ክልል (ቢኤአርኤምኤም) እንዲመሰረት አስችለዋል፡፡

Skip to content